የገዛ ራሱም ምድር ጊዜ እስኪመጣ ድረስ አሕዛብ ሁሉ ለእርሱና ለልጁ ለልጅ ልጁም ይገዛሉ፤ በዚያን ጊዜም ብዙ አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት ለእርሱ ይገዙለታል።
ኤርምያስ 46:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር እንደሚመጣና የግብፅን ምድር እንደሚመታ እግዚአብሔር ለነቢዩ ለኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር መጥቶ ግብጽን እንደሚወጋ፣ እግዚአብሔር ለነቢዩ ለኤርምያስ የተናገረው መልእክት ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር እንደሚመጣና የግብጽን ምድር እንደሚመታ ጌታ ለነቢዩ ለኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በግብጽ ላይ አደጋ ለመጣል ስለ መምጣቱ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር እንዲመጣና የግብጽን ምድር እንዲመታ እግዚአብሔር ለነቢዩ ለኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው። |
የገዛ ራሱም ምድር ጊዜ እስኪመጣ ድረስ አሕዛብ ሁሉ ለእርሱና ለልጁ ለልጅ ልጁም ይገዛሉ፤ በዚያን ጊዜም ብዙ አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት ለእርሱ ይገዙለታል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ጠላቱ ለሆነው፥ ነፍሱንም ለፈለገው ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እንደ ሰጠሁት፥ እንዲሁ እነሆ የግብፅን ንጉሥ ፈርዖን ሖፍራን ለጠላቶቹ፥ ነፍሱንም ለሚፈልጉ እጅ አሳልፌ እሰጠዋለሁ።
“ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ሰይፍን አመጣብሃለሁ፦ ሰውንና እንስሳንም ከአንተ ዘንድ አጠፋለሁ።