La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 42:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ስለ​ዚህ እና​ንተ የይ​ሁዳ ቅሬታ ሆይ! አሁን እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወደ ግብ​ፅም ትገቡ ዘንድ በዚ​ያም ትቀ​መጡ ዘንድ ፊታ​ች​ሁን ብታ​ቀኑ፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንግዲህ የይሁዳ ቅሬታ ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ወደ ግብጽ ለመሄድ ወስናችሁ እዚያ ለመቀመጥ ብትሄዱ፣

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እናንተ የይሁዳ ትሩፍ ሆይ! እንግዲህ አሁን የጌታን ቃል ስሙ፤ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ወደ ግብጽ ለመግባት በዚያም ሄዳችሁ ለመቀመጥ በእርግጥ ፊታችሁን ብታቀኑ፥

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እናንተ የይሁዳ ቅሬታ ሆይ! እግዚአብሔር ስለ እናንተ የሚለውን ስሙ፤ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ወደ ግብጽ ወርዳችሁ በዚያ ለመኖር ብትወስኑ፥

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እናንተ የይሁዳ ቅሬታ ሆይ፥ አሁን እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ግብጽ ትገቡ ዘንድ በዚያም ትቀመጡ ዘንድ ፊታችሁን ብታቀኑ፥

Ver Capítulo



ኤርምያስ 42:15
8 Referencias Cruzadas  

እር​ሱም ያለ​ውን ሁሉ ይዞ ኰበ​ለለ፤ ተነ​ሥ​ቶም ወን​ዙን ተሻ​ገረ፤ በገ​ለ​ዓድ ተራ​ራም አደረ።


“ለባ​ቢ​ሎን ንጉ​ሥም ለና​ቡ​ከ​ን​ደ​ነ​ፆር የማ​ይ​ገ​ዛ​ውን፥ ከባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ቀን​በር በታች አን​ገ​ቱን ዝቅ የማ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ሕዝ​ብና መን​ግ​ሥት፥ ያን ሕዝብ በእጁ እስ​ካ​ጠ​ፋው ድረስ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም እቀ​ጣ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ወደ ግብ​ፅም ይገቡ ዘንድ፥ በዚ​ያም ይቀ​መጡ ዘንድ ፊታ​ቸ​ውን በሚ​ያ​ቀኑ ሰዎች ሁሉ እን​ዲህ ይሆ​ን​ባ​ቸ​ዋል፤ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም ያል​ቃሉ፤ እኔም ከማ​መ​ጣ​ባ​ቸው ክፉ ነገር ማንም አይ​ቀ​ርም፤ ማንም አያ​መ​ል​ጥም።


ኤር​ም​ያ​ስም ለሕ​ዝቡ ሁሉ፥ ለሴ​ቶ​ቹም ሁሉ እን​ዲህ አለ፥ “በግ​ብፅ ምድር የም​ት​ኖሩ አይ​ሁድ ሁሉ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


የመ​ው​ጣቱ ወራ​ትም በቀ​ረበ ጊዜ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ለመ​ሄድ ፊቱን አቀና።


ለእ​ርሱ ፈረ​ሶ​ችን እን​ዳ​ያ​በዛ፥ ሕዝ​ቡ​ንም ወደ ግብፅ እን​ዳ​ይ​መ​ልስ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በዚ​ያች መን​ገድ መመ​ለ​ስን አት​ድ​ገም ብሎ​አ​ልና።