የሠራዊቱም አለቆች ሁሉ ሰዎቻቸውም፥ የናታንዩ ልጅ እስማኤል፥ የቃሬያን ልጅ ዮሐናን፥ የነጦፋዊውም የተንሑሜት ልጅ ሴሪያ፥ የማዕካታዊው ልጅ አዛንያ፥ ሰዎቻቸውም የባቢሎን ንጉሥ ጎዶልያን እንደ ሾመው በሰሙ ጊዜ ወደ ጎዶልያ ወደ መሴፋ መጡ።
ኤርምያስ 41:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቃርሔም ልጅ ዮሐናን፥ ከእርሱም ጋር የነበሩ የጭፍራ አለቆች ሁሉ የናታንያ ልጅ እስማኤል ያደረገውን ክፋት ሁሉ ሰሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቃሬያ ልጅ ዮሐናና ከርሱ ጋራ የነበሩት የጦር መኰንኖች ሁሉ የናታንያ ልጅ እስማኤል የፈጸመውን ግፍ ሁሉ በሰሙ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቃሬያም ልጅ ዮሐናን ከእርሱም ጋር የነበሩ የጭፍራ አለቆች ሁሉ የናታንያ ልጅ እስማኤል ያደረገውን ክፋት ሁሉ በሰሙ ጊዜ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሐናንና ከእርሱ ጋር የነበሩት የሠራዊት መሪዎች ሁሉ እስማኤል የፈጸመውን ወንጀል ሰሙ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቃሬያም ልጅ ዮሐናን ከእርሱም ጋር የነበሩ የጭፍራ አለቆች ሁሉ የናታንያ ልጅ እስማኤል ያደረገውን ክፋት ሁሉ በሰሙ ጊዜ፥ |
የሠራዊቱም አለቆች ሁሉ ሰዎቻቸውም፥ የናታንዩ ልጅ እስማኤል፥ የቃሬያን ልጅ ዮሐናን፥ የነጦፋዊውም የተንሑሜት ልጅ ሴሪያ፥ የማዕካታዊው ልጅ አዛንያ፥ ሰዎቻቸውም የባቢሎን ንጉሥ ጎዶልያን እንደ ሾመው በሰሙ ጊዜ ወደ ጎዶልያ ወደ መሴፋ መጡ።
ወደ ከተማም መካከል በመጡ ጊዜ የናታንያ ልጅ እስማኤል፥ ከእርሱም ጋር የነበሩ ሰዎች ገደሉአቸው፤ በጕድጓድም መካከል ጣሉአቸው።
የጭፍራ አለቆችም ሁሉ፥ የቃርሔም ልጅ ዮሐናን፥ የሐናንያ ልጅ ኢዛንያስ ሕዝቡም ሁሉ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ መጡ።