ኤርምያስ 4:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ለይሁዳ ወንዶችና ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እንዲህ ይላልና፦ ልባችሁን አድሱ በእሾህም ላይ አትዝሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ሰዎች እንዲህ ይላል፤ “ዕዳሪውን መሬት ዕረሱ፤ በእሾኽም መካከል አትዝሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ሰዎች እንዲህ ይላልና፦ “ያልታረሰ መሬታችሁን እረሱ በእሾህም ላይ አትዝሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እንዲህ ይላል፦ “እዳሪውን መሬት እረሱ፤ ዘራችሁን በሾኽ መካከል አትዝሩ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ሰዎች እንዲህ ይላልና፦ ጥጋቱን እርሻ እረሱ በእሾህም ላይ አትዝሩ። |
በሰባተኛው ዓመት ግን ተዋት፤ አሳርፋትም፤ የሕዝብህም ድሆች ይበሉታል፤ እነርሱ ያስቀሩትንም የሜዳ እንስሳ ይብላው። እንዲሁም በወይንህና በወይራህ አድርግ።
ለእናንተ ጽድቅን ዝሩ፤ የሕይወት ፍሬን ሰብስቡ፤ የጥበብንም ብርሃን ለራሳችሁ አብሩ፤ የጽድቃችሁ መከር እስኪደርስ እግዚአብሔርን ፈልጉት።
በእሾህም መካከል የወደቀው ቃሉን ሰምተው የባለጠግነት ዐሳብ፥ የኑሮም መቈርቈር የተድላና የደስታ መጣፈጥም የሚአስጨንቃቸውና ፍሬ የማያፈሩ ናቸው።