ኤርምያስ 4:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተመለከትሁ፤ እነሆም ቀርሜሎስ ምድረ በዳ ሆነች፤ ከተሞችም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊት የተነሣ በእሳት ተቃጠሉ፤ ከጽኑ ቍጣውም የተነሣ ፈጽመው ጠፉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተመለከትሁ፤ እነሆም፣ ፍሬያማው ምድር በረሓ ሆነ፤ ከተሞቹ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት፣ ከብርቱ ቍጣው የተነሣ ፈራረሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አየሁ፥ እነሆም፥ ፍሬያማው እርሻ ምድረ በዳ ሆኖ፥ ከተሞችም ሁሉ ከጌታ ፊት ከጽኑ ቁጣው የተነሣ ፈርሰው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለምለሚቱ ምድር ወደ በረሓነት ተለውጣለች፤ ከእግዚአብሔር ብርቱ ቊጣ የተነሣ፥ ከተሞችዋ ሁሉ ፈራርሰዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አየሁ፥ እነሆም፥ ፍሬያማ እርሻ ምድረ በዳ ሆነች፥ ከተሞችም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊት ከጽኑ ቍጣው የተነሣ ፈርሰው ነበር። |
ስንዴን ትዘራላችሁ፤ እሾህንም ታጭዳላችሁ፤ ዕጣችሁም ምንም አይጠቅማችሁም፤ ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ የተነሣ በአዝመራችሁ ታፍራላችሁ።
በሚኖሩባት ሰዎች ክፋት ምድሪቱ የምታለቅሰውና የዱሩ ሣርስ ሁሉ የሚደርቀው እስከ መቼ ነው? እግዚአብሔር ፍጻሜያችንን አያይም ብለዋልና እንስሶችና ወፎችም ጠፍተዋል።
ምድሪቱም ባድማ ትሆናለችና ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም አደባባይ የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፥ የወንድ ሙሽራን ድምፅና የሴት ሙሽራን ድምፅ አጠፋለሁ።
በተራሮቹ ላይ አልቅሱ፤ በምድረ በዳም ጎዳና ላይ እዘኑ፤ ሰው ጠፍትዋልና፤ የሚመላለስም የለምና ሙሾውንም አሙሹ፤ የሰማይ ወፍ ድምፅንም እስከ ከብት ድምፅ ድረስ አይሰሙም፤ ደንግጠውም ተማርከው ሄዱ።
ዛይ። እግዚአብሔር መሠዊያውን ጣለ፤ መቅደሱንም ጠላው፤ የአዳራሾችዋንም ቅጥር በጠላት እጅ ሰበረ። እንደ ዓመት በዓል ቀን በእግዚአብሔር ቤት ድምፃቸውን በዕልልታ አሰሙ።
ከተሞቻችሁንም ባድማ አደርጋለሁ፤ መቅደሶቻችሁንም አፈርሳለሁ፤ የመሥዋዕታችሁንም መዓዛ አላሸትትም።
በእግዚአብሔርም ቍጣ ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፣ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ፈጥኖ ይጨርሳቸዋልና ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች።