ኤርምያስ 39:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በግዞት ቤቱ አደባባይም ታስሮ ሳለ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤርምያስ በዘበኞች አደባባይ ታስሮ በነበረበት ጊዜ፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እርሱ እንዲህ ሲል መጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእስር ቤትም አደባባይ ታስሮ ሳለ የጌታ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቤተ መንግሥቱ አደባባይ በእስራት ላይ ሳለሁ የእግዚአብሔር ቃል ወደኔ መጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በግዞትም ቤት አደባባይ ታስሮ ሳለ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ |
ንጉሡም ሴዴቅያስ አዘዘ፤ ኤርምያስንም በግዞት ቤቱ ቅጥር ግቢ አኖሩት፤ እንጀራም ሁሉ ከከተማ እስኪጠፋ ድረስ ዕለት ዕለት አንድ አንድ እንጀራ ከውጪ ጋጋሪዎች እያመጡ ይሰጡት ነበር። እንዲሁም ኤርምያስ በግዞት ቤት ቅጥር ግቢ ተቀምጦ ነበር።
ኤርምያስንም ከግዞት ቤቱ አደባባይ አወጡት፤ ወደ ቤቱም ይወስደው ዘንድ ለሳፋን ልጅ ለአኪቃም ልጅ ለጎዶልያስ ሰጡት፤ እንዲህም በሕዝብ መካከል ተቀመጠ።