La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 38:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አቤ​ሜ​ሌ​ክም ከእ​ርሱ ጋር ሰዎ​ችን ይዞ ሄደ፤ ከቤተ መዛ​ግ​ብ​ቱም በታች ወደ ነበ​ረው ወደ ንጉሥ ቤት ገባ፤ ከዚ​ያም ዕላቂ ጨር​ቅና አሮጌ ገመድ ወሰደ፥ ወደ ኤር​ም​ያ​ስም ወደ ጕድ​ጓዱ ውስጥ በገ​መድ አወ​ረ​ደው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አቢሜሌክም ሰዎቹን ይዞ በቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤት ሥር ወዳለው ክፍል ሄደ፤ ያረጀ ጨርቅና ያለቀ ልብስ ከዚያ ወስዶ ወደ ኤርምያስ ወደ ጕድጓዱ ውስጥ በገመድ አወረደለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አቤሜሌክም ከእርሱ ጋር ሰዎችን ይዞ ሄደ፥ ከቤተ መዛግብቱም በታች ወደነበረው ወደ ንጉሥ ቤት ገባ፥ ከዚያም አሮጌ ጨርቅና እላቂ ልብስ ወሰደ፥ ወደ ኤርምያስም ወደ ጉድጓድ ውስጥ በገመድ አወረደው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህም አቤሜሌክ ሰዎቹን አስከትሎ ሄደ፤ ወደ ቤተ መንግሥቱ ዕቃ ግምጃ ቤትም ገብቶ ወፍራም ጨርቅና አሮጌ ልብስ አገኘ፤ እርሱንም በገመድ አስሮ ሰደደልኝ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አቤሜሌክም ከእርሱ ጋር ሰዎችን ይዞ ሄደ፥ ከቤተ መዛግብቱም በታች ወደ ነበረው ወደ ንጉሥ ቤት ገባ፥ ከዚያም አሮጌ ጨርቅና እላቂ ልብስ ወሰደ፥ ወደ ኤርምያስም ወደ ጉድጓድ ውስጥ በገመድ አወረደው።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 38:11
5 Referencias Cruzadas  

ንጉ​ሡም ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ዊ​ዉን አቤ​ሜ​ሌ​ክን፥ “ከአ​ንተ ጋር ሠላሳ ሰዎች ከዚህ ውሰድ፤ ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስም ሳይ​ሞት ከጕ​ድ​ጓድ አው​ጣው” ብሎ አዘ​ዘው።


ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ዊ​ውም አቤ​ሜ​ሌክ ኤር​ም​ያ​ስን፥ “እነ​ዚ​ህን ጨር​ቆች በብ​ብ​ትህ ከገ​መዱ በታች አድ​ርግ” አለው፤ ኤር​ም​ያ​ስም እን​ዲሁ አደ​ረገ።


ኤር​ም​ያ​ስ​ንም ወሰ​ዱት፤ በግ​ዞት ቤትም አደ​ባ​ባይ ወደ ነበ​ረው ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መል​ክያ ጕድ​ጓድ ውስጥ ጣሉት፤ ኤር​ም​ያ​ስ​ንም በገ​መድ አወ​ረ​ዱት። በጕ​ድ​ጓ​ዱም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውኃ አል​ነ​በ​ረ​በ​ትም፤ ኤር​ም​ያ​ስም ወደ ጭቃው ውስጥ ገባ።


በን​ጉ​ሡም ቤት የነ​በ​ረው ጃን​ደ​ረባ ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ዊው አቤ​ሜ​ሌክ ኤር​ም​ያ​ስን በጕ​ድ​ጓድ ውስጥ እንደ ጣሉት ሰማ።


ነገር ግን ብርና ወርቅ ሁሉ፥ የና​ስና የብ​ረ​ትም ዕቃ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ይሁን፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግምጃ ቤት ይግባ።”