Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 38:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 አቤሜሌክም ከእርሱ ጋር ሰዎችን ይዞ ሄደ፥ ከቤተ መዛግብቱም በታች ወደነበረው ወደ ንጉሥ ቤት ገባ፥ ከዚያም አሮጌ ጨርቅና እላቂ ልብስ ወሰደ፥ ወደ ኤርምያስም ወደ ጉድጓድ ውስጥ በገመድ አወረደው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 አቢሜሌክም ሰዎቹን ይዞ በቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤት ሥር ወዳለው ክፍል ሄደ፤ ያረጀ ጨርቅና ያለቀ ልብስ ከዚያ ወስዶ ወደ ኤርምያስ ወደ ጕድጓዱ ውስጥ በገመድ አወረደለት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ስለዚህም አቤሜሌክ ሰዎቹን አስከትሎ ሄደ፤ ወደ ቤተ መንግሥቱ ዕቃ ግምጃ ቤትም ገብቶ ወፍራም ጨርቅና አሮጌ ልብስ አገኘ፤ እርሱንም በገመድ አስሮ ሰደደልኝ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 አቤ​ሜ​ሌ​ክም ከእ​ርሱ ጋር ሰዎ​ችን ይዞ ሄደ፤ ከቤተ መዛ​ግ​ብ​ቱም በታች ወደ ነበ​ረው ወደ ንጉሥ ቤት ገባ፤ ከዚ​ያም ዕላቂ ጨር​ቅና አሮጌ ገመድ ወሰደ፥ ወደ ኤር​ም​ያ​ስም ወደ ጕድ​ጓዱ ውስጥ በገ​መድ አወ​ረ​ደው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 አቤሜሌክም ከእርሱ ጋር ሰዎችን ይዞ ሄደ፥ ከቤተ መዛግብቱም በታች ወደ ነበረው ወደ ንጉሥ ቤት ገባ፥ ከዚያም አሮጌ ጨርቅና እላቂ ልብስ ወሰደ፥ ወደ ኤርምያስም ወደ ጉድጓድ ውስጥ በገመድ አወረደው።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 38:11
5 Referencias Cruzadas  

ንጉሡም ኢትዮጵያዊውን አቤሜሌክን፦ “ከአንተ ጋር ሠላሳ ሰዎች ከዚህ ውሰድ፥ ነቢዩም ኤርምያስ ሳይሞት ከጉድጓድ አውጣው” ብሎ አዘዘው።


ኢትዮጵያዊውም አቤሜሌክ ኤርምያስን፦ “ይህን አሮጌ ጨርቅና እላቂውን ልብስ በብብትህ ከገመዱ በታች አድርግ” አለው፤ ኤርምያስም እንዲሁ አደረገ።


ኤርምያስንም ወሰዱት፤ በእስር ቤቱም አደባባይ ወደነበረው ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መልክያ ጉድጓድ ውስጥ ኤርምያስን በገመድ አውርደው ጣሉት። በጉድጓድም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውኃ አልነበረበትም፤ ኤርምያስም ወደ ጭቃው ውስጥ ገባ።


በንጉሡም ቤት የነበረው ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ አቤሜሌክ ኤርምያስን በጉድጓዱ ውስጥ እንዳኖሩት ሰማ። ንጉሡም በብንያም በር ተቀምጦ ነበር።


ነገር ግን ብርና ወርቅ ሁሉ የናስና የብረትም ዕቃ ለጌታ የተቀደሰ ይሁን፤ ወደ ጌታም ግምጃ ቤት ይግባ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos