ኤርምያስ 38:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ኢትዮጵያዊዉን አቤሜሌክን፥ “ከአንተ ጋር ሠላሳ ሰዎች ከዚህ ውሰድ፤ ነቢዩ ኤርምያስም ሳይሞት ከጕድጓድ አውጣው” ብሎ አዘዘው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም ኢትዮጵያዊውን አቢሜሌክን፣ “ሠላሳ ሰዎች ከዚህ ይዘህ ሂድ፤ ነቢዩ ኤርምያስንም ሳይሞት ከጕድጓድ አውጣው” ብሎ አዘዘው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ኢትዮጵያዊውን አቤሜሌክን፦ “ከአንተ ጋር ሠላሳ ሰዎች ከዚህ ውሰድ፥ ነቢዩም ኤርምያስ ሳይሞት ከጉድጓድ አውጣው” ብሎ አዘዘው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኢትዮጵያዊውን አቤሜሌክን “ከዚህ ሠላሳ ሰዎች ይዘህ ሂድና ነቢዩ ኤርምያስን ከመሞቱ በፊት ከውሃው ጒድጓድ አውጡት” ሲል አዘዘው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ኢትዮጵያዊውን አቤሜሌክን፦ ከአንተ ጋር ሠላሳ ሰዎች ከዚህ ውሰድ፥ ነቢዩም ኤርምያስ ሳይሞት ከጕድጓድ አውጣው ብሎ አዘዘው። |
አቤሜሌክም ከእርሱ ጋር ሰዎችን ይዞ ሄደ፤ ከቤተ መዛግብቱም በታች ወደ ነበረው ወደ ንጉሥ ቤት ገባ፤ ከዚያም ዕላቂ ጨርቅና አሮጌ ገመድ ወሰደ፥ ወደ ኤርምያስም ወደ ጕድጓዱ ውስጥ በገመድ አወረደው።
“ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ነቢዩን ኤርምያስን በጕድጓድ ውስጥ በመጣላቸው በእርሱ ላይ በአደረጉት ሁሉ ክፉ አድርገዋል፤ በከተማዪቱም ውስጥ እንጀራ ስለሌለ በዚያ በራብ ይሞታል።”