Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 38:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኢትዮጵያዊውን አቤሜሌክን “ከዚህ ሠላሳ ሰዎች ይዘህ ሂድና ነቢዩ ኤርምያስን ከመሞቱ በፊት ከውሃው ጒድጓድ አውጡት” ሲል አዘዘው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ንጉሡም ኢትዮጵያዊውን አቢሜሌክን፣ “ሠላሳ ሰዎች ከዚህ ይዘህ ሂድ፤ ነቢዩ ኤርምያስንም ሳይሞት ከጕድጓድ አውጣው” ብሎ አዘዘው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ንጉሡም ኢትዮጵያዊውን አቤሜሌክን፦ “ከአንተ ጋር ሠላሳ ሰዎች ከዚህ ውሰድ፥ ነቢዩም ኤርምያስ ሳይሞት ከጉድጓድ አውጣው” ብሎ አዘዘው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ንጉ​ሡም ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ዊ​ዉን አቤ​ሜ​ሌ​ክን፥ “ከአ​ንተ ጋር ሠላሳ ሰዎች ከዚህ ውሰድ፤ ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስም ሳይ​ሞት ከጕ​ድ​ጓድ አው​ጣው” ብሎ አዘ​ዘው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ንጉሡም ኢትዮጵያዊውን አቤሜሌክን፦ ከአንተ ጋር ሠላሳ ሰዎች ከዚህ ውሰድ፥ ነቢዩም ኤርምያስ ሳይሞት ከጕድጓድ አውጣው ብሎ አዘዘው።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 38:10
7 Referencias Cruzadas  

ንጉሡ፥ ንግሥት አስቴር በስተ ውጪ በኩል መቆምዋን በተመለከተ ጊዜ በፊቱ ሞገስን አግኝታ ስለ ነበር የወርቅ በትሩን ዘረጋላት፤ እርስዋም ቀረብ ብላ የወርቁን በትር ጫፍ ነካች።


ከዚህም በኋላ ንጉሥ አርጤክስስ ንግሥት አስቴርንና አይሁዳዊውን መርዶክዮስን እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ ሃማን በአይሁድ ላይ ስለ ፈጸመው ሤራ በእንጨት ላይ እንዳሰቀልኩትና ሀብቱንም ሁሉ ለአስቴር እንደ ሰጠሁ የሚታወስ ነው፤


እርሱ የክፉዎችን ኀይል ይሰብራል፤ የጻድቃን ኀይል ግን እየጨመረ ይሄዳል።


የንጉሥ ልብ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ እርሱንም እንደ ወራጅ ውሃ ወደ ፈቀደው ይመራዋል። የንጉሥንም አእምሮ ይቈጣጠራል።


ስለዚህም አቤሜሌክ ሰዎቹን አስከትሎ ሄደ፤ ወደ ቤተ መንግሥቱ ዕቃ ግምጃ ቤትም ገብቶ ወፍራም ጨርቅና አሮጌ ልብስ አገኘ፤ እርሱንም በገመድ አስሮ ሰደደልኝ።


የሆነ ሆኖ አቤሜሌክ ተብሎ የሚጠራ በቤተ መንግሥቱ ያገለግል የነበረ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ እኔን ወደ ጒድጓድ ውስጥ እንደ ከተቱኝ ሰማ፤ በዚያን ጊዜ ንጉሡ በብንያም ቅጽር በር ሸንጎ ተቀምጦ ነበር፤


“ንጉሥ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ታላቅ በደል ፈጽመዋል፤ እነሆ ኤርምያስን ጒድጓድ ውስጥ ከተውታል፤ በከተማይቱ ምግብ ስለሌለ እዚያው በረሀብ መሞቱ ነው።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos