ኤርምያስ 37:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አይሄዱምና፦ ከለዳውያን በርግጥ ከእኛ ዘንድ ይሄዳሉ ብላችሁ ራሳችሁን አታታልሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ባቢሎናውያን በርግጥ ትተውን ይሄዳሉ’ ብላችሁ አታስቡ፤ አይሄዱምና ራሳችሁን አታታልሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ ይላል፦ አይሄዱምና፦ “ከለዳውያን በእርግጥ ከእኛ ዘንድ ይሄዳሉ” ብላችሁ ራሳችሁን አታታሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘ባቢሎናውያን ተመልሰው ይሄዳሉ’ ብላችሁ ራሳችሁን አታታሉ፤ እነርሱ ተመልሰው አይሄዱም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አይሄዱምና፦ ከለዳውያን በእርግጥ ከእኛ ዘንድ ይሄዳሉ ብላችሁ ራሳችሁን አታታልሉ። |
የእስራኤልም አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ “በመካከላችሁ ያሉት የሐሰት ነቢያቶቻችሁና ምዋርተኞቻችሁ አያታልሉአችሁ፤ ሕልም አላሚዎች አለምንላችሁ የሚሉአችሁን አትስሙ፥
በተሰነጠቀም ዓለት ውስጥ እንደሚኖር- ማደሪያውንም ከፍ ከፍ እንደሚያደርግ፥ በልቡም፦ ወደ ምድር የሚያወርደኝ ማን ነው? እንደሚል፥ የልብህ ትዕቢት እጅግ አኵርቶሃል።
በከንቱ ነገርም የሚያስታችሁ አይኑር፤ በእርሱ ምክንያት በከሓዲዎች ልጆች ላይ የእግዚአብሔር መዓት ይመጣልና።