የይሁዳም ንጉሥ ዮአኪን ከእናቱ፥ ከብላቴኖቹም፥ ከአለቆቹም፥ ከጃንደረቦቹም ጋር ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወጣ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ያዘው።
ኤርምያስ 37:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በይሁዳ ያነገሠው የኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ በኢዮአቄም ልጅ በኢኮንያን ፋንታ ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የኢዮስያስን ልጅ ሴዴቅያስን በይሁዳ ላይ አነገሠው፤ እርሱም በኢዮአቄም ልጅ በኢኮንያን ፈንታ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር በይሁዳ ምድር ላይ ያነገሠው የኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ በኢዮአቄም ልጅ በኢኮንያን ፋንታ ነገሠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የኢዮስያስን ልጅ ሴዴቅያስን የኢዮአቄም ልጅ በነበረው በኢኮንያን ምትክ በይሁዳ ላይ አነገሠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር በይሁዳ ያነገሠው የኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ በኢዮአቄም ልጅ በኢኮንያን ፋንታ ነገሠ። |
የይሁዳም ንጉሥ ዮአኪን ከእናቱ፥ ከብላቴኖቹም፥ ከአለቆቹም፥ ከጃንደረቦቹም ጋር ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወጣ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ያዘው።
የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ የመልክያን ልጅ ጳስኮርንና የካህኑን የመዕሴይን ልጅ ሶፎንያስን ወደ ኤርምያስ በላከ ጊዜ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦ እንዲህም አለ፦
“እኔ ሕያው ነኝ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአቄም ልጅ ኢኮንያን ሆይ፥ አንተን በሰወርሁበት ቀኝ እጄ እንዳለ ማሕተም ነበርህ፤ እንግዲህ ወዲህ ግን እንደማትኖር እኔ ሕያው ነኝ፤” ይላል እግዚአብሔር፤
ኢኮንያን ተዋረደ፤ ለምንም እንደማይጠቅም የሸክላ ዕቃ ሆነ፤ እርሱንና ዘሩን ወደማያውቀው ሀገር ወርውረው ጥለውታልና።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን፥ የይሁዳንም አለቆች፥ ብልሃተኞችንና እስረኞችን፥ ጓደኞቻቸውንም ከኢየሩሳሌም ማርኮ ወደ ባቢሎን ከአፈለሳቸው በኋላ፥ እነሆ እግዚአብሔር በእግዚአብሔር መቅደስ ፊት የተቀመጡ ሁለት የበለስ ቅርጫቶችን አሳየኝ።
“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሂድ፤ ለይሁዳም ንጉሥ ለሴዴቅያስ ተናገር፤ እንዲህም በለው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ይች ከተማ በባቢሎን ንጉሥ እጅ ተላልፋ ትሰጣለች፤ ይይዛታል፤ በእሳትም ያቃጥላታል።
እንዲህም ሆነ፤ የይሁዳ ንጉሥ ኢኮንያን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት፥ በዐሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያ አምስተኛው ቀን፥ የባቢሎን ንጉሥ ዮርማሮዴቅ በነገሠ በአንደኛው ዓመት የይሁዳን ንጉሥ የኢኮንያንን ራስ ከፍ ከፍ አደረገ፤ ከወህኒም አወጣው፤