La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 34:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ነገር ግን በሰ​ላም ትሞ​ታ​ለህ፥ ከአ​ንተ በፊት እንደ ነበሩ እንደ ዱሮ ነገ​ሥ​ታት አባ​ቶ​ችህ እሳት ይቃ​ጠ​ል​ላ​ቸው እንደ ነበር እን​ዲሁ ያቃ​ጥ​ሉ​ል​ሃ​ልና፦ ወየው! ጌታ ሆይ! እያሉ ያለ​ቅ​ሱ​ል​ሃል፤ እኔ ቃልን ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በሰላም ትሞታለህ። ሕዝቡ ከአንተ በፊት ለነበሩት ነገሥታት አባቶችህ ክብር በቀብራቸው ጊዜ እሳት እንዳነደዱ፣ በቀብርህም ጊዜ ስለ ክብርህ እሳት ያነድዳሉ፤ “ዋይ ዋይ ጌታችን!” እያሉም ያለቅሱልሃል፤ እኔ ራሴ ይህን ቃል ተናግሬአለሁና፤ ይላል እግዚአብሔር።’ ”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በሰላም ትሞታለህ። ከአንተ በፊት እንደ ነበሩ እንደ ዱሮ ነገሥታት እንደ አባቶችህ ዕጣን እንደታጠነላቸው፥ እንዲሁ ለአንተም ዕጣንን ያጥኑልሃል፦ “ወየው! ጌታ ሆይ!” እያሉ ያለቅሱልሃል፤’ እኔ ቃልን ተናግሬአለሁና፥ ይላል ጌታ።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በሰላም ታርፋለህ፤ ከአንተ በፊት ነገሥታት የነበሩ የቀድሞ አባቶችህ በሞቱ ጊዜ ሕዝቡ ለክብራቸው እሳት ያነዱላቸው እንደ ነበር ለአንተም እንዲሁ እሳት ያነዱልሃል፤ ‘ወዮ ንጉሣችን፥’ እያሉም ያለቅሱልሃል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከአንተ በፊት እንደ ነበሩ እንደ ዱሮ ነገሥታት እንደ አባቶችህ መቃጠል፥ እንዲሁ ያቃጥሉሃልና፦ ወየው! ጌታ ሆይ እያሉ ያለቅሱልሃል፥ እኔ ቃልን ተናግሬአለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 34:5
10 Referencias Cruzadas  

ነገሩ እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ ወደ አባ​ቶ​ችህ እሰ​በ​ስ​ብ​ሃ​ለሁ፥ በሰ​ላ​ምም ወደ መቃ​ብ​ርህ ትሰ​በ​ሰ​ባ​ለህ፤ በዚ​ህም ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ የማ​መ​ጣ​ውን ክፉ ነገር ዐይ​ኖ​ችህ አያ​ዩም።” ይህ​ንም ለን​ጉሡ ነገ​ሩት።


ለእ​ር​ሱም ለራሱ በሠ​ራው መቃ​ብር በዳ​ዊት ከተማ ቀበ​ሩት፤ በቀ​ማሚ ብል​ሃት የተ​ሰ​ናዳ ልዩ ልዩ መል​ካም ሽቱ በተ​ሞላ አልጋ ላይም አኖ​ሩት፤ እጅ​ግም ታላቅ የሆነ የቀ​ብር ሥር​ዐት አደ​ረ​ጉ​ለት።


እነሆ፥ ወደ አባ​ቶ​ችህ እሰ​በ​ስ​ብ​ሃ​ለሁ፤ በሰ​ላ​ምም ወደ መቃ​ብ​ርህ ትሰ​በ​ሰ​ባ​ለህ፤ በዚ​ህም ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ የማ​መ​ጣ​ውን ክፉ ነገር ሁሉ ዐይ​ኖ​ችህ አያ​ዩም” ያለ​ቻ​ቸ​ው​ንም ነገር ለን​ጉሡ አስ​ረ​ዱት።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮ​ስ​ያስ ልጅ ስለ ኢዮ​አ​ቄም እን​ዲህ ይላል፥ “ወን​ድሜ ሆይ፥ ወዮ! ጌታዬ ሆይ፥ ወዮ! እያለ የሚ​ያ​ለ​ቅ​ስ​ለት ለሌ​ለው ለዚያ ሰው ወዮ​ለት!


“ነገር ግን የይ​ሁዳ ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አንተ እን​ዲህ ይላል፦ በሰ​ይፍ አት​ሞ​ትም፤


ሬስ። ስለ እርሱ፥ “በአ​ሕ​ዛብ ውስጥ በጥ​ላው በሕ​ይ​ወት እን​ኖ​ራ​ለን” ያል​ነው፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀባ፥ የሕ​ይ​ወ​ታ​ችን እስ​ት​ን​ፋስ፥ በወ​ጥ​መ​ዳ​ቸው ተያዘ።


“እኔ ሕያው ነኝ! ያነ​ገ​ሠ​ውና መሐ​ላ​ውን የና​ቀ​በት፥ ቃል ኪዳ​ኑ​ንም ያፈ​ረ​ሰ​በት ንጉሥ በሚ​ኖ​ር​በት ስፍራ ከእ​ርሱ ጋር በባ​ቢ​ሎን መካ​ከል በር​ግጥ ይሞ​ታል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


የሳ​ኦ​ል​ንም ሬሳ፥ የልጁ የዮ​ና​ታ​ን​ንም ሬሳ ከቤ​ት​ሶም ቅጥር ላይ አወ​ረዱ፤ ወደ ኢያ​ቢ​ስም አመ​ጡ​አ​ቸው፤ በዚ​ያም አቃ​ጠ​ሉ​አ​ቸው።