ኤርምያስ 33:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ቀንና ሌሊት በወራታቸው እንዳይሆኑ የቀን ቃል ኪዳኔንና የሌሊት ቃል ኪዳኔን ማፍረስ ብትችሉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ለቀንና ለሌሊት የወሰንሁትን ሥርዐት በማፋለስ ቀንና ሌሊት በተወሰነላቸው ጊዜ እንዳይፈራረቁ ኪዳኔን ማፍረስ ብትችሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታ እንዲህ ይላል፦ ቀንና ሌሊት በተመደበላቸው ጊዜ እንዳይሆኑ የቀን ቃል ኪዳኔንና የሌሊት ቃል ኪዳኔን ማፍረስ ብትችሉ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለአገልጋዬ ለዳዊት ዙፋን የሚወርስ ልጅ እንደምሰጠው የገባሁት ቃል ኪዳንና ለአገልጋዮቼ ለሌዋውያን ስለሚሰጡኝ አገልግሎት ያቆምኩላቸው ቃል ኪዳን ሊፈርሱ የሚችሉት ቀንና ሌሊት በተወሰነላቸው ጊዜ እንዲመጡ ያቆምኩላቸውን ሥርዓት ከእናንተ መካከል ለማፍረስ የሚችል ሰው የተገኘ ከሆነው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ቀንና ሌሊት በወራቱ እንዳይሆን የቀን ቃል ኪዳኔንና የሌሊት ቃል ኪዳኔን ማፍረስ ብትችሉ፥ |
“እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር በፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፥ እንዲሁ ዘራችሁና ስማችሁ ጸንተው ይኖራሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።
ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ነኝና እነርሱ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ፥ እስካጠፋቸው ድረስ ከእነርሱም ጋር ያለኝን ቃል ኪዳን እስካፈርስ ድረስ አልጥላቸውም፤ አልጸየፋቸውምም።