ነፍሴ የወደደችህ አንተ ንገረኝ፤ በባልንጀሮችህ መንጎች መካከል የተቅበዘበዝሁ እንዳልሆን፥ ወዴት ታሰማራለህ? በቀትርስ ጊዜ ወዴት ትመሰጋለህ?
ኤርምያስ 33:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ባድማ ሆኖ፥ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ባለው በዚህ ስፍራ በከተሞችም ሁሉ መንጎቻቸውን የሚያሳርፉበት የእረኞች መኖሪያ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ሰውም ሆነ እንስሳት በማይኖሩበት በዚህ ባዶ ስፍራ፣ በከተማዎቹም ሁሉ እረኞች መንጎቻቸውን የሚያሳርፉበት እንደ ገና ያገኛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ባድማ ሆና፥ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ በሆነችው በዚህች ስፍራ፥ በከተሞችዋም ሁሉ መንጎቻቸውን የሚያሳርፉ የእረኞች መኖሪያ ስፍራ ዳግመኛ ይኖራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ሕዝብም ሆነ እንስሳ የማይኖርባት ምድረ በዳ በሆነች በዚህች ምድር እንደገና እረኞች የበጎቻቸውን መንጋ የሚያሠማሩበት መስክ ይኖራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ባድማ ሆኖ፥ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ባለው በዚህ ስፍራ በከተሞችም ሁሉ መንጎቻቸውን የሚያሳርፉት የእረኞች መኖሪያ ይሆናል። |
ነፍሴ የወደደችህ አንተ ንገረኝ፤ በባልንጀሮችህ መንጎች መካከል የተቅበዘበዝሁ እንዳልሆን፥ ወዴት ታሰማራለህ? በቀትርስ ጊዜ ወዴት ትመሰጋለህ?
የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉንም ቍርባን፥ እጅ መንሻውንና ዕጣኑን፥ የምስጋናውንም መሥዋዕት ይዘው ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም ዙሪያ፥ ከብንያምም ሀገር፥ ከቆላውም፥ ከደጋውም፥ ከደቡብም ወደ እግዚአብሔር ቤት ይመጣሉ።
ይመጣሉ፤ በጽዮንም ተራራ ደስ ይላቸዋል፤ ወደ እግዚአብሔርም በጎነት፥ ወደ እህልና ወደ ወይን ጠጅ፥ ወደ ዘይትም፥ ወደ በጎችና ወደ ላሞች ሀገርም ይሰበሰባሉ፤ ነፍሳቸውም እንደ ረካች ገነት ትሆናለች፤ ከእንግዲህም ወዲህ አይራቡም።
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰዎች በዚህ ምድር ቤትንና እርሻን የወይን ቦታንም እንደ ገና ይገዛሉ።”
የይሁዳንም ንጉሥ ኢዮአቄምን እንዲህ በለው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አንተ፦ የባቢሎን ንጉሥ በርግጥ ይመጣል፤ ይችንም ሀገር ያፈርሳታል፤ ሰውና እንስሳም ያልቃሉ ብለህ ለምን ጻፍህበት? ብለህ ይህን ክርታስ አቃጥለሃል።
“ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነዋል፤ እረኞቻቸው አሳቱአቸው፤ በተራሮችም ላይ የተቅበዘበዙ አደረጉአቸው፤ ከተራራ ወደ ኮረብታ ዐለፉ፤ በረታቸውንም ረሱ።
አቤቱ! ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ማንም እንዳይቀመጥባት፥ ለዘለዓለምም ባድማ እንድትሆን ታጠፋት ዘንድ በዚች ስፍራ ላይ ተናግረሃል በል።
ሰዎችም ባድማ የነበረች ይህች ምድር እንደ ዔድን ገነት ሆናለች፤ የፈረሱት፥ ባድማ የሆኑት፥ የጠፉትም ከተሞች ተመሽገዋል፤ ሰውም የሚኖርባቸው ሆነዋል ይላሉ።