ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል፥ ከአንተም በኋላ በዘርህ መካከል በትውልዳቸው ለዘለዓለም ኪዳን አቆማለሁ፤ ለአንተና ከአንተም በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።
ኤርምያስ 32:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱ ሕዝብ ይሆኑኛል፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ። |
ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል፥ ከአንተም በኋላ በዘርህ መካከል በትውልዳቸው ለዘለዓለም ኪዳን አቆማለሁ፤ ለአንተና ከአንተም በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።
እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ የሚያውቅ ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ በፍጹምም ልባቸው ወደ እኔ ይመለሳሉና ሕዝቤ ይሆኑኛል፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።”
ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።
ነገር ግን በሕፃንነትሽ ወራት ከአንቺ ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳኔን ዐስባለሁ፤ የዘለዓለምንም ቃል ኪዳን አጸናልሻለሁ።
እኔም ወደ አሕዛብ አስማርኬአቸዋለሁና፥ ወደ ገዛ ምድራቸውም ሰብስቤአቸዋለሁና እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ በዚያም ከእነርሱ አንድ ሰው ከእንግዲህ ወዲያ አላስቀርም፤
ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።
በዘመንህም ሁሉ አምላክህን እግዚአብሔርን መፍራትን ትማር ዘንድ፥ ስሙ እንዲጠራበት በመረጠው ስፍራ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት የእህልህን፥ የወይንህን፥ የዘይትህንም ዐሥራት፥ የላምህንና የበግህንም በኵራት ብላ።
አሁን ግን፥ በሰማያት ያለችውን የምትበልጠውን ሀገር ተስፋ ያደርጉ እንደ ነበር ታወቀ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ይጠራ ዘንድ በእነርሱ አያፍርም፤ ተስፋ ያደረጉአትን ሀገር አዘጋጅቶላቸዋልና።
ከእነዚያ ዘመናት በኋላ ለቤተ እስራኤል የምገባው ቃል ይህ ነው፦ ሕጌን በልባቸው አሳድራለሁ፤ በሕሊናቸውም እጽፈዋለሁ፤ አምላክ እሆናቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆኑኛል ይላል እግዚአብሔር።