የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰዎች በዚህ ምድር ቤትንና እርሻን የወይን ቦታንም እንደ ገና ይገዛሉ።”
ኤርምያስ 31:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ገናም በሰማርያ ተራሮች ላይ የወይን ተክሎችን ትተክሊአለሽ፤ የምትተክሉ ትከሉ፤ አመስግኑም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ገናም በሰማርያ ኰረብቶች ላይ፣ ወይን ትተክያለሽ፤ አትክልተኞች ይተክሏቸዋል፤ በፍሬውም ደስ ይላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደገናም በሰማርያ ተራሮች ላይ ወይንን በወይን እርሻዎች ትተክዪአለሽ፤ አትክልተኞች ይተክላሉ እነርሱም በፍሬው ይደሰታሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደገናም በሰማርያ ኰረብቶች ላይ ወይን ትተክዪአለሽ ፍሬውንም የደከሙበት ሰዎች ይበሉታል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ገናም በሰማርያ ተራሮች ላይ የወይን ቦታዎችን ትተክሊአለሽ፥ አትክልተኞች ይተክላሉ በፍሬውም ደስ ይላቸዋል። |
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰዎች በዚህ ምድር ቤትንና እርሻን የወይን ቦታንም እንደ ገና ይገዛሉ።”
ተዘልለውም ይቀመጡባታል፤ ቤቶችንም ይሠራሉ፤ ወይኑንም ይተክላሉ፤ በዙሪያቸውም በአሉ በሚንቋቸው ሁሉ ላይ ፍርድን በአደረግሁ ጊዜ ተዘልለው ይቀመጣሉ፤ እኔም እግዚአብሔር አምላካቸው፥ የአባቶቻቸውም አምላክ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
የሕዝቤን የእስራኤልን ምርኮ እመልሳለሁ፤ የፈረሱትንም ከተሞች ሠርተው ይቀመጡባቸዋል፤ ወይንንም ይተክላሉ፤ የወይን ጠጃቸውንም ይጠጣሉ፤ ተክልን ይተክላሉ፤ ፍሬውንም ይበላሉ።
የደቡብም ሰዎች የዔሳውን ተራራ፥ የቆላውም ሰዎች ፍልስጥኤማውያንን ይወርሳሉ፤ የኤፍሬምንም ተራራ፥ የሰማርያን፥ የብንያምንና የገለዓድን ሀገር ይወርሳሉ።
ስለዚህ ሰማርያን በሜዳ እንደሚገኝ የድንጋይ ክምር፥ ወይን እንደሚተከልበትም ስፍራ አደርጋታለሁ፥ ድንጋዮችዋንም ወደ ሸለቆ እወረውራለሁ፥ መሠረቶችዋንም እገልጣለሁ።
ወይንም ተክሎ ደስ ያልተሰኘበት ሰው ቢኖር በጦርነት እንዳይሞት ሌላም ሰው ደስ እንዳይሰኝበት ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ።
ሚስት ታገባለህ፤ ሌላም ሰው ይነጥቅሃል፤ ቤት ትሠራለህ፤ በእርሱም አትቀመጥበትም፤ ወይን ትተክላለህ፤ ከእርሱም አትለቅምም።
ዳዊትም ለካህኑ መልሶ፥ “ከሴቶች ተለይተን ወደ መንገድ ከወጣን ዛሬ ሦስተኛ ቀናችን ነው። እኔም ብላቴኖቼም ንጹሓን ነን። ነገር ግን ዛሬ ሰውነቴ ንጽሕት ስለ ሆነች ነው እንጂ ይህች መንገድ የነጻች አይደለችም” አለው።