ኤርምያስ 29:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገሩላችኋልና፤ እኔም አልላክኋቸውም፥” ይላል እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በስሜ ሐሰተኛ ትንቢት ይነግሯችኋል እንጂ እኔ አልላክኋቸውም” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ለእናንተ ይናገራሉ፤ እኔም አላክኋቸውም፥ ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ በእኔ ስም የሚነግሩአችሁ ትንቢት ሁሉ ሐሰት ነው፤ እኔ ከቶ አላክኋቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገሩላችኋልና፥ እኔም አልላክኋቸውም። |
እኔ አልላክኋቸውምና፤ ነገር ግን እኔ እንዳሳድዳችሁ፥ እናንተና ትንቢት የሚናገሩላችሁ ነቢያትም እንድትጠፉ በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገራሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።”
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ስለሚናገሩላችሁ ስለ ቆልያ ልጅ፥ ስለ አክዓብና ሰለ ማሴው ልጅ ስለ ሴዴቅያስ እንዲህ ይላል፥ “እነሆ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ በዐይኖቻችሁም ፊት ይገድላቸዋል።
በእስራኤል ዘንድ ክፉ አድርገዋልና፥ ከባልንጀሮቻቸውም ሚስቶች ጋር አመንዝረዋልና፥ ያላዘዝኋቸውንም ቃል በስሜ በሐሰት ተናግረዋልና። እኔም አውቃለሁ፤ ምስክርም ነኝ፥ ይላል እግዚአብሔር።”
“እግዚአብሔር ስለ አሔልማዊው ስለ ሸማያ እንዲህ ይላል ብለህ ወደ ምርኮኞች ሁሉ ላክ፦ እኔ ሳልልከው ሸማያ ትንቢት ተናግሮላችኋልና፥ በሐሰትም እንድትታመኑ አድርጓችኋልና።
ኖን። ነቢያትሽ ከንቱና ዕብደትን አይተውልሻል፤ ምርኮሽን ይመልሱ ዘንድ በደልሽን አልገለጡም፤ ከንቱና የማይረባ ነገርንም አይተውልሻል።