ኤርምያስ 29:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁንም አጋቡ፤ እነርሱም ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ይውለዱ፤ ከዚያም ተባዙ፤ ጥቂቶችም አትሁኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አግብታችሁ ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ውለዱ፤ ወንዶች ልጆቻችሁንና ሴቶች ልጆቻችሁን አጋቡ፤ እነርሱም ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ይውለዱ፤ ቍጥራችሁም በዚያ ምድር ይብዛ እንጂ አይነስ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተጋቡ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ውለዱ፤ ሴቶች ልጆቻችሁንም ለወንዶች ልጆቻችሁ አጋቡ፥ እነርሱም ወንዶችንና ሴቶችን ልጆች ይውለዱ፤ በዚያም ተባዙ ጥቂቶችም አትሁኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እየተጋባችሁ ልጆችን ውለዱ፤ ልጆቻችሁም በተራቸው እየተጋቡ ልጆችን ይውለዱ፤ ቊጥራችሁ ይብዛ እንጂ አይቀንስ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተጋቡ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ውለዱ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁንም አጋቡ፥ እነርሱም ወንዶችንና ሴቶችን ልጆች ይውለዱ፥ ከዚያም ተባዙ ጥቂቶችም አትሁኑ። |
እኅታቸው ርብቃንም መረቁአትና፥ “አንቺ እኅታችን፥ እልፍ አእላፋት ሁኚ፤ ዘርሽም የጠላት ሀገሮችን ይውረስ” አሉአት።
እንግዲህ ቆነጃጅት ሊያገቡ፥ ልጆችንም ሊወልዱ፥ ቤቶቻቸውንም ሊያስተዳድሩ፥ ተቃዋሚውም የሚሳደብበትን አንድን ምክንያት ስንኳ እንዳይሰጡ እፈቅዳለሁ፤
ሠላሳ ወንዶች ልጆችና ሠላሳ ሴቶች ልጆችንም ወለደ፤ ሠላሳ ሴቶች ልጆቹንም ወደ ውጭ ሀገር ዳረ፤ ለወንዶች ልጆቹም ከውጭ ሀገር ሠላሳ ሴቶች ልጆችን አመጣ። እስራኤልንም ሰባት ዓመት ገዛ።
ወጥቶም ለአባቱና ለእናቱ፥ “በቴምናታ ከፍልስጥኤማውያን ልጆች አንዲት ሴት አይቻለሁ፤ አሁንም እርስዋን አጋቡኝ” አላቸው።