የእግዚአብሔርን ቤተ መዛግብት ሁሉ የንጉሡንም ቤተ መዛግብት ከዚያ አወጣ፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር መቅደስ የሠራውን የወርቁን ዕቃ ሁሉ ሰባበረ።
ኤርምያስ 27:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለካህናትም ለዚህም ሕዝብ እንዲህ ብዬ ተናገርሁ፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሐሰተኛውን ትንቢት ይናገሩላችኋልና፦ የእግዚአብሔር ቤት ዕቃ በቅርብ ጊዜ ከባቢሎን ይመለሳል የሚሉአችሁን የነቢያቶቻችሁን ቃል አትስሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም ለካህናቱና ለዚህ ሕዝብ ሁሉ እንዲህ አልሁ፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘የእግዚአብሔር ቤት ዕቃ ከባቢሎን ቶሎ ይመለሳል’ የሚሏችሁን ነቢያት አትስሟቸው፤ የሚነግሯችሁ የሐሰት ትንቢት ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለካህናትም ለዚህም ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ብዬ ተናገርሁ፦ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሐሰተኛን ትንቢት ለእናንተ በመናገር፦ ‘እነሆ፥ የጌታ ቤት ዕቃዎች በቅርብ ጊዜ ከባቢሎን ይመለሳሉ’ ብለው ትንቢት የሚነግሩአችሁን የነብዮቻችሁን ቃላት አትስሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ለካህናቱና ለሕዝቡ እንዳስታውቅ እግዚአብሔር የሚከተለውን ነገረኝ፤ እንዲህ ብዬም ነገርኳቸው፦ “ ‘የቤተ መቅደሱ ዕቃ ሁሉ ከባቢሎን ተመልሶ በፍጥነት ይመጣል’ እያሉ የሚነግሩአችሁን ነቢያት ሁሉ አትስሙአቸው፤ እነርሱ የሚናገሩት የሐሰት ትንቢት ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለካህናትም ለዚህም ሕዝብ እንዲህ ብዬ ተናገርሁ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሐሰተኛውን ትንቢት ይናገሩላችኋልና፦ የእግዚአብሔር ቤት ዕቃ በቅርብ ጊዜ ከባቢሎን ይመለሳል የሚሉአችሁን የነቢያቶቻችሁን ቃል አትስሙ። |
የእግዚአብሔርን ቤተ መዛግብት ሁሉ የንጉሡንም ቤተ መዛግብት ከዚያ አወጣ፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር መቅደስ የሠራውን የወርቁን ዕቃ ሁሉ ሰባበረ።
ከምድራችሁ እንዲያርቁአችሁ፥ እኔም እንዳሳድዳችሁ፥ እናንተም እንድትጠፉ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገሩላችኋልና።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከዚች ስፍራ ወደ ባቢሎን የወሰዳቸውን የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃዎች ሁሉ በሁለት ዓመት ውስጥ ወደዚህች ስፍራ እመልሳለሁ፤