ሴዴቅያስም በነገሠ ጊዜ ሃያ አንድ ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም አሚጣል የተባለች የሎብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።
ኤርምያስ 27:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም መንግሥት መጀመሪያ ይህ ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በይሁዳ ንጉሥ፣ በኢዮስያስ ልጅ በሴዴቅያስ ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ ላይ ይህ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም መንግሥት መጀመሪያ ይህ ቃል ከጌታ ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ በይሁዳ ከነገሠ በኋላ ወዲያውኑ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም መንግሥት መጀመሪያ ይህ ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ። |
ሴዴቅያስም በነገሠ ጊዜ ሃያ አንድ ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም አሚጣል የተባለች የሎብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።
ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስም ይህን ቃል ሁሉ ተናገርሁ፥ “ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች አንገታችሁን ዝቅ አድርጉ፤ ለእርሱና ለሕዝቡም ተገዙላቸው በሕይወትም ኑሩ።
ወደ ይሁዳ ንጉሥም ወደ ሴዴቅያስ፥ ወደ ኢየሩሳሌም በመጡት መልእክተኞች እጅ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ፥ ወደ ሞዓብም ንጉሥ፥ ወደ አሞን ልጆች ንጉሥ፥ ወደ ጢሮስም ንጉሥ፥ ወደ ሲዶናም ንጉሥ ላክ።”
ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ፤ በዚያ ዓመት፥ በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ መንግሥት መጀመሪያ፥ በአራተኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ሐሰተኛው ነቢይ የገባዖን ሰው የዓዙር ልጅ ሐናንያ በእግዚአብሔር ቤት በካህናትና በሕዝብ ሁሉ ፊት እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦
በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ በዐሥረኛው ዓመተ መንግሥት፥ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በዐሥራ ስምንተኛው ዓመተ መንግሥት ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።