ኤርምያስ 25:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድዳንንም፥ ቴማንንም፥ ሮስንም፥ ፊታቸውን የሚከተቡትን ሁሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድዳንን፣ ቴማንን፣ ቡዝን፣ ጠጕራቸውን ዙሪያውን የሚከረከሙትን ሕዝብ ሁሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድዳንንም፥ ቴማንንም፥ ቡዝንም፥ የጠጉራቸውንም ማዕዘን የሚቈርጡትን ሁሉ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድዳንንም፥ ቴማንንም፥ ቡዝንም፥ ጠጕራቸውንም የሚቈርጡትን ሁሉ፥ |
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ መታቸው ስለ ቄዳርና ስለ አሦር መንግሥታት እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ተነሡ ወደ ቄዳርም ውጡ፤ የምሥራቅንም ልጆች አጥፉ።
ግመሎቻቸው ለምርኮ ይሆናሉ፤ የእንስሶቻቸውም ብዛት ለጥፋት ይሆናል፤ ጠጕራቸውንም በዙሪያ የሚላጩትን ሰዎች ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናቸዋለሁ፤ ከዳርቻቸው ሁሉ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር፥
ስለ ኤዶምያስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በውኑ በቴማን ጥበብ የለምን? ከብልሃተኞችስ ምክር ጠፍቶአልን? ጥበባቸውስ አልቆአልን?
እናንተ በድዳን የምትኖሩ ሆይ! የዔሳውን ጥፋት፥ የምጐበኝበትን ጊዜ አመጣበታለሁና ሽሹ፤ ወደ ኋላም ተመለሱ፤ በጥልቅም ጕድጓድ ውስጥ ተቀመጡ።
አሕዛብ ሁሉ ያልተገረዙ ናቸውና፥ የእስራኤልም ቤት ሁሉ ልባቸው ያልተገረዘ ነውና የተገረዙትን ሁሉ፥ ግብጽንና ይሁዳን፥ ኤዶምያስንም፥ የአሞንንም ልጆች፥ ሞዓብንም፥ በምድረ በዳም የተቀመጡትን ጠጕራቸውን በዙሪያ የተላጩትንም ሁሉ የምጐበኝበት ዘመን እነሆ ይመጣል።”
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እጄን በኤዶምያስ ላይ እዘረጋለሁ፤ ከእርስዋም ዘንድ ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤ ባድማም አደርጋታለሁ፤ ከቴማንና ከድዳንም ያመለጡ በሰይፍ ይወድቃሉ።
የሮድያን ልጆችም ነጋዴዎችሽ ነበሩ፥ ብዙ የሆኑ የደስያት ሰዎችም የዝኆን ጥርስ ይነግዱልሽ ነበር፤ ከዚያም የመጡ ሰዎች ዋጋሽን ይሰጡሽ ነበር።