እግዚአብሔር ግን እንደ ኀያል ተዋጊ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆች ይሰናከላሉ፤ አያሸንፉም፤ ለዘለዓለምም የማይረሳ ጕስቍልናቸውን አላወቁምና ፈጽመው አፈሩ።
ኤርምያስ 23:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዘለዓለምንም ስድብና ከቶ ተረስቶ የማይጠፋውን የዘለዓለምን ውርደት አመጣባችኋለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለዘላለም የማይረሳ ዕፍረት፣ የዘላለምም ውርደት አመጣባችኋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዘለዓለምንም ስድብ፥ ከቶም ተረስቶ የማይጠፋውን የዘለዓለምን እፍረት አመጣባችኋለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእነርሱም ላይ ከቶ የማይረሳ ዘለዓለማዊ ኀፍረትና ውርደት አመጣባቸዋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዘላለምንም ስድብ ከቶም ተረስቶ የማይጠፋውን የዘላለምን እፍረት አመጣባችኋለሁ። |
እግዚአብሔር ግን እንደ ኀያል ተዋጊ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆች ይሰናከላሉ፤ አያሸንፉም፤ ለዘለዓለምም የማይረሳ ጕስቍልናቸውን አላወቁምና ፈጽመው አፈሩ።
በማሳድዳቸውም ስፍራ ሁሉ ለስድብና ለምሳሌ፥ ለጥላቻና ለርግማን ይሆኑ ዘንድ በምድር መንግሥታት ሁሉ እንዲበተኑ አደርጋለሁ።
“የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ቍጣዬና መቅሠፍቴ በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ላይ እንደ ፈሰሰ፥ እንዲሁ ወደ ግብፅ በገባችሁ ጊዜ መዓቴ ይፈስስባችኋል፤ እናንተም ለጥላቻና ለጥፋት ለስድብና ለርግማን ትሆናላችሁ፤ ይችንም ስፍራ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩአትም።
አሁንም ከእነርሱ ይልቅ አብዝተሽ በሠራሽው ኀጢአትሽ እኅቶችሽን ስላረከስሻቸው ቅጣትሽን ተሸከሚ። ከአንቺም ይልቅ አጸደቅሻቸው፤ አንችም እፈሪ፤ እፍረትሽንም ተሸከሚ፤ እኅቶችሽን አጽድቀሻቸዋልና።