Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 23:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 በእነርሱም ላይ ከቶ የማይረሳ ዘለዓለማዊ ኀፍረትና ውርደት አመጣባቸዋለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 ለዘላለም የማይረሳ ዕፍረት፣ የዘላለምም ውርደት አመጣባችኋለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 የዘለዓለምንም ስድብ፥ ከቶም ተረስቶ የማይጠፋውን የዘለዓለምን እፍረት አመጣባችኋለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 የዘ​ለ​ዓ​ለ​ም​ንም ስድ​ብና ከቶ ተረ​ስቶ የማ​ይ​ጠ​ፋ​ውን የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምን ውር​ደት አመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 የዘላለምንም ስድብ ከቶም ተረስቶ የማይጠፋውን የዘላለምን እፍረት አመጣባችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 23:40
10 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ግን እንደ ጀግና ወታደር ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ በመደናቀፍ ኀይል አጥተው ይወድቃሉ። በሚወድቁበትም ጊዜ ክፉኛ ይዋረዳሉ፤ ውርደታቸውም ለረጅም ጊዜ ይታወሳል።


በስደት እንዲበታተኑ ባደረግሁባቸው በምድር መንግሥታት ሁሉ ዘንድ የተጠሉ፥ የተሰደቡ፥ የመነጋገሪያ ርእስ የሆኑ፥ መሳለቂያና የተወገዙ እንዲሆኑ አደርጋቸዋለሁ።


“የሠራዊት ጌታ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ወደ ግብጽ እንሄዳለን ብላችሁ ብትወስኑ ከዚህ በፊት በኢየሩሳሌም ሕዝብ ላይ የወረደው ቊጣዬና መዓቴ በእናንተም ላይ ይወርዳል፤ ለሕዝብ ሁሉ አስፈሪ መቀጣጫ ትሆናላችሁ፤ የሚያዩአችሁም ሕዝብ ሁሉ መዘባበቻ ያደርጓችኋል፤ ስማችሁም ለመሳለቂያ ይሆናል፤ ይህችንም ስፍራ ዳግመኛ አታዩአትም።’ ”


እነሆ አሁንም ውርደትሽን ተሸከሚ፤ የአንቺ ኃጢአት እጅግ የከፋ ከመሆኑ የተነሣ እኅቶችሽ ከአንቺ ጋር ሲነጻጸሩ ምንም በደል የሌለባቸው ንጹሖች መስለው ይታያሉ፤ አሁንም እኅቶችሽን በደል የሌለባቸው ንጹሖች እንዲመስሉ በማድረግሽ ኀፍረትን እንደ ልብስ ተከናንበሽ ተቀመጪ።”


ሞተው ዐፈር የበላቸው ሁሉ ይነሣሉ፤ ከእነርሱም ከፊሎቹ ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት ሲገቡ ከፊሎቹ ደግሞ ወደ ዘለዓለማዊ ኀፍረትና ውርደት ይላካሉ።


ጌታ ሆይ! ስለ ፈጸምካቸው የጽድቅ ሥራዎች ሁሉ ብለህ ከተቀደሰችው ተራራህ ከኢየሩሳሌም ቊጣህንና መዓትህን እንድታነሣ እንለምንሃለን፤ በኃጢአታችንና በአባቶቻችንም በደል ምክንያት ኢየሩሳሌምና ሕዝብህ በጐረቤቶቻችን ሁሉ መካከል ተዋርደዋል።


“እናንተ ካህናት ቊጥራችሁ በበዛ መጠን በደላችሁም በፊቴ እየበዛ ሄዶአል፤ ስለዚህ ክብራችሁን ገፍፌ አዋርዳችኋለሁ።


እግዚአብሔር በሚበትንህ አገሮች የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ላይ የደረሰውን ነገር አይተው ይደነግጣሉ፤ መቀለጃና መዘባበቻም ያደርጉሃል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos