በእርሱም ዘመን የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ኒካዑ ከአሦር ንጉሥ ጋር ሊጋጠም ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ወጣ፤ ንጉሡም ኢዮስያስ ከእርሱ ጋር ሊጋጠም ወጣ፤ ፈርዖንም በተገናኘው ጊዜ በመጊዶ ገደለው።
ኤርምያስ 22:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአባቱ በኢዮስያስ ፋንታ ስለ ነገሠው፥ ከዚህም ስፍራ ስለ ወጣውና ስለማይመለሰው ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ፥ ስለ ሳሌም እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአባቱ ምትክ በይሁዳ ላይ ስለ ነገሠው፣ ከዚህ ስፍራ በምርኮ ስለ ተወሰደው፣ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ሰሎ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ “ከእንግዲህ አይመለስም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአባቱ በኢዮስያስ ፋንታ ስለ ነገሠው ከዚህም ስፍራ ስለ ወጣው ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ሰሎም ጌታ እንዲህ ይላልና፦ “ዳግመኛ ወደዚህ አይመለስም፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአባቱ ምትክ በይሁዳ ስለ ነገሠው ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ሻሉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ዳግመኛ ወደማይመለስበት ወደ ሩቅ አገር ይሄዳል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአባቱ በኢዮስያስ ፋንታ ስለ ነገሠው ከዚህም ስፍራ ስለ ወጣው ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ሰሎም እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ |
በእርሱም ዘመን የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ኒካዑ ከአሦር ንጉሥ ጋር ሊጋጠም ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ወጣ፤ ንጉሡም ኢዮስያስ ከእርሱ ጋር ሊጋጠም ወጣ፤ ፈርዖንም በተገናኘው ጊዜ በመጊዶ ገደለው።
አገልጋዮቹም በድኑን በሰረገላው አድርገው ከመጊዶ ወደ ኢየሩሳሌም አመጡት፤ በመቃብሩም ቀበሩት። የሀገሩም ሰዎች የኢዮስያስን ልጅ ዮአክስን ወሰዱት። ቀብተውም በአባቱ ፋንታ አነገሡት።
ዮአክስም በነገሠ ጊዜ ሃያ ሦስት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወር ነገሠ። እናቱም አሚጣል ትባል ነበር፥ እርስዋም የሎብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።
ፈርዖን ኒካዑም የይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስን ልጅ ኤልያቄምን በአባቱ በኢዮስያስ ፋንታ አነገሠ፤ ስሙንም ኢዮአቄም ብሎ ለወጠው። ዮአክስንም ወስዶ ወደ ግብፅ አፈለሰው፤ በዚያም ሞተ።
ደግሞም ከኤፍሬም ልጆች አለቆች የአናን ልጅ ዓዛርያስ፥ የመስለሞት ልጅ በራክያ፥ የሳሎም ልጅ ሕዝቅያስ፥ የአዳሊ ልጅ አማስያ ከሰልፍ የተመለሱትን ተቃወሙአቸው።
ኬልቅያስና እነዚያ ንጉሡ ያዘዛቸው ወደ ልብስ ጠባቂው ወደ ሐስራ ልጅ ወደ ቴቁዋ ልጅ ወደ ሴሌም ሚስት ወደ ነቢይቱ ወደ ሕልዳና ሄዱ፤ እርስዋም በኢየሩሳሌም በከተማዪቱ በሁለተኛው ክፍል ተቀምጣ ነበር፤ ይህንም ነገር ነገሩአት።
በይሁዳ ንጉሥ በአሞጽ ልጅ በኢዮስያስ ዘመን ወደ ሕዝቅያስ ልጅ ወደ አማርያ ልጅ ወደ ጎዶልያስ ልጅ ወደ ኵሲ ልጅ ወደ ሶፎንያስ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።