ኤርምያስ 2:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንቺ ግን፦ ንጹሕ ነኝ፤ በእውነት ቍጣው ከእኔ ይመለስ አልሽ። እነሆ ኀጢአት አልሠራሁም ብለሻልና እፋረድሻለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘እኔ ንጹሕ ነኝ፤ በርግጥ ቍጣው ከእኔ ርቋል’ ትያለሽ። እኔ ግን እፈርድብሻለሁ፤ ‘ኀጢአት አልሠራሁም’ ብለሻልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንቺ ግን፦ ‘እኔ ንጹሕ ነኝ፤ በእውነት ቁጣው ከእኔ ተመልሶአል’ አልሽ። እነሆ፦ ‘ኃጢአት አልሠራሁም’ ብለሻልና በፍርድ እከስሻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንቺ ግን፦ ንጹሕ ነኝ፥ በእውነት ቍጣው ከእኔ ተመልሶአል አልሽ። እነሆ፦ ኃጢአት አልሠራሁም ብለሻልና በፍርድ እከስስሻለሁ። |
“ስለ ምን ጾምን፥ አንተም አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለ ምን አዋረድን፥ አንተም አላወቅኸንም?” ይላሉ። እነሆ፥ በጾማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፥ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ።
“ለዚህም ሕዝብ ይህን ቃል ሁሉ በተናገርህ ጊዜ፦ ይህን ሁሉ ትልቅ የሆነ ክፉ ነገርን ስለ ምን እግዚአብሔር ተናገረብን? በደላችንስ ምንድን ነው? በአምላካችንስ በእግዚአብሔር ፊት ያደረግነው ኀጢአት ምንድን ነው? ቢሉህ፥
አንቺስ፦ አልረከስሁም፤ በዓሊምንም አልተከተልሁም፤ እንዴት ትያለሽ? በሸለቆ ያለውን መንገድሽን ተመልከቺ፤ ያደረግሽውንም ዕወቂ። ማታ ማታ በመንገዶች ትጮኻለች፤
እግዚአብሔር ከአሕዛብ ጋር ክርክር አለውና ጥፋት እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይደርሳል፤ ከሥጋ ለባሽ ሁሉም ጋር ይፋረዳል፤ ኀጢአተኞችንም ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል፥ ይላል እግዚአብሔር።”
መረቤንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ፤ በወጥመድም ይያዛል፤ ወደ ባቢሎንም አመጣዋለሁ፤ በእኔም ላይ ስላደረገው ዐመፅ በዚያ ከእርሱ ጋር እፋረዳለሁ።