Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 2:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 “ስለ​ዚህ እንደ ገና ከእ​ና​ንተ ጋር እከ​ራ​ከ​ራ​ለሁ፤ ከል​ጆ​ቻ​ች​ሁም ልጆች ጋር እከ​ራ​ከ​ራ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “ስለዚህ እንደ ገና ከእናንተ ጋራ እፋረዳለሁ፤ ከልጅ ልጆቻችሁም ጋራ እከራከራለሁ።” ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 “ስለዚህ ከእናንተ ጋር ገና እከራከራለሁ፥ ይላል ጌታ፥ ከልጆቻችሁም ልጆች ጋር እከራከራለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “ስለዚህ እኔ እግዚአብሔር ገና እናንተን ሕዝቤን እወቅሳለሁ፤ በልጆቻችሁም ላይ ወቀሳ አቀርባለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ስለዚህ ከእናንተ ጋር እከራከራለሁ፥ ከልጆቻችሁም ልጆች ጋር እከራከራለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 2:9
12 Referencias Cruzadas  

አን​ተን ብቻ በደ​ልሁ፥ በፊ​ት​ህም ክፋ​ትን አደ​ረ​ግሁ፥ በነ​ገ​ርህ ትጸ​ድቅ ዘንድ በፍ​ር​ድ​ህም ታሸ​ንፍ ዘንድ።


አት​ስ​ገ​ድ​ላ​ቸው፤ አታ​ም​ል​ካ​ቸ​ውም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ቀና​ተኛ አም​ላክ ነኝና። በሚ​ጠ​ሉኝ እስከ ሦስ​ተ​ኛና አራ​ተኛ ትው​ልድ ድረስ የአ​ባ​ቶ​ችን ኀጢ​አት በል​ጆች ላይ የማ​መጣ፤


ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ለፍ​ርድ ይነ​ሣል፤ በሕ​ዝ​ቡም ላይ ሊፈ​ርድ ይነ​ሣል።


አሳ​ስ​በኝ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ሆነን እን​ፋ​ረድ፤ እን​ድ​ት​ጸ​ድቅ አስ​ቀ​ድ​መህ በደ​ል​ህን ተና​ገር።


“ከእኔ ጋር ለምን ትከ​ራ​ከ​ራ​ላ​ችሁ? ሁላ​ችሁ ክዳ​ች​ሁ​ኛል፤ ሁላ​ች​ሁም ዐም​ፃ​ች​ሁ​ብ​ኛል” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


አንቺ ግን፦ ንጹሕ ነኝ፤ በእ​ው​ነት ቍጣው ከእኔ ይመ​ለስ አልሽ። እነሆ ኀጢ​አት አል​ሠ​ራ​ሁም ብለ​ሻ​ልና እፋ​ረ​ድ​ሻ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደግሞ ከይ​ሁዳ ጋር ይዋ​ቀ​ሳል፤ ያዕ​ቆ​ብ​ንም እንደ መን​ገዱ ይበ​ቀ​ለ​ዋል፤ እንደ ሥራ​ውም ይከ​ፍ​ለ​ዋል።


እና​ታ​ችሁ ሚስቴ አይ​ደ​ለ​ች​ምና፥ እኔም ባልዋ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምና እና​ታ​ች​ሁን ተዋ​ቀ​ሱ​አት። ዝሙ​ቷን ከፊቷ፥ ምን​ዝ​ር​ና​ዋ​ንም ከጡ​ቶ​ችዋ መካ​ከል አስ​ወ​ግ​ዳ​ለሁ።


እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ! እው​ነ​ትና ምሕ​ረት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ማወቅ በም​ድር ስለ​ሌለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ላይ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ይወ​ቅ​ሳ​ልና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


እር​ሱ​ንና ከሞ​ሎክ ጋር ያመ​ነ​ዝሩ ዘንድ የሚ​ከ​ተ​ሉ​ትን ሁሉ ከሕ​ዝ​ባ​ቸው መካ​ከል ለይች አጠ​ፋ​ለሁ።


ተራሮች ሆይ፥ ጠንካሮች የምድር መሠረቶችም ሆይ፥ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ክርክር አለውና፥ ከእስራኤልም ጋር ይፋረዳልና የእግዚአብሔርን ክርክር ስሙ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos