ኤርምያስ 2:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በውኑ እስራኤል ባሪያ ነውን? ወይስ የቤት ውላጅ ነውን? ስለ ምን ምርኮ ሆነ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤል ባሪያ ነውን? ወይስ የቤት ውልድ ባሪያ? ታዲያ፣ ስለ ምን ለብዝበዛ ተዳረገ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በውኑ እስራኤል ባርያ ነውን? ወይስ በቤት የተወለደ አገልጋይ ነውን? ስለምን ለብዝበዛ ሆነ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እስራኤል የተገዛች ባሪያ አይደለችም፤ የቤት ውልድም ባሪያ አይደለችም፤ ታዲያ፥ ጠላቶችዋ (በምርኮ እንደ አውሬ የሚያድኑአት) ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ እስራኤል ባሪያ ነውን? ወይስ የቤት ውላጅ ነውን? ስለምን ብዝበዛ ሆነ? |
ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮችን ገዛሁ፤ በቤት የተወለዱ አገልጋዮችም ነበሩኝ፤ ከእኔ አስቀድመው በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ብዙ የበጎችና የከብቶች መንጋዎች ነበሩኝ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እናታችሁን የፈታሁበት የፍችዋ ደብዳቤ የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለማን ነው? እነሆ፥ ስለ ኀጢአታችሁ ተሸጣችኋል፤ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈትታለች።
አንተም የሰጠሁህን ርስት ትለቅቃለህ፤ ለዘለዓለምም በማታውቃት ምድር ለጠላቶችህ አስገዛሃለሁ፤ ቍጣዬ ለዘለዓለም እንደ እሳት ትነድዳለችና።
እንዲህም ይሆናል፤ እናንተ፥ “አምላካችን እግዚአብሔር ይህን ነገር ሁሉ ስለ ምን አደረገብን?” ብትሉ፥ አንተ፥ “እንደ ተዋችሁኝ፥ በሀገራችሁም ሌሎችን አማልክት እንዳመለካችሁ፥ እንዲሁ ለእናንተ ባልሆነ ሀገር ለሌሎች ሰዎች ትገዛላችሁ” ትላቸዋለህ።