ወንድሞቹና እኅቶቹ ቀድሞም ያውቁት የነበሩት ሁሉ የሆነውን ሁሉ በሰሙ ጊዜ ወደ እርሱ መጡ፥ በቤቱም ከእርሱ ጋር እንጀራ በሉ፥ ጠጡም፤ አጽናኑትም፤ እግዚአብሔርም ባመጣበት ክፉ ነገር ሁሉ አደነቁ፤ እያንዳንዳቸውም ጥማድ በሬ፥ አራት ድራህማ የሚመዝን ወርቅና ብር ሰጡት።
ኤርምያስ 16:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰዎችም ስለ ሞቱት ለማጽናናት የእዝን እንጀራ አይቈርሱላቸውም፤ ስለ አባታቸውና ስለ እናታቸውም የመጽናናት ጽዋ አያጠጡአቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐዘንተኞችን ለማጽናናት የዕዝን እንጀራ የሚያመጣ አይኖርም፤ አባትም ሆነ እናት የሞተባቸውንም ለማጽናናት መጠጥ የሚያቀርብ አይገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰዎችም ስለ ሞቱት ለማጽናናት የኀዝን እንጀራ አይቈርሱላቸውም፥ ስለ አባታቸውና ስለ እናታቸውም የመጽናናት ጽዋ አያጠጡአቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወዳጁ የሞተበትን ሰው ለማጽናናት የእዝን እንጀራ በመውሰድ አብሮት የሚበላና የሚጠጣ አይኖርም፤ ሌላው ቀርቶ እናትም አባትም የሞቱበትን የሚያጽናና አይገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰዎችም ስለ ሞቱት ለማጽናናት የእዝን እንጀራ አይቈርሱላቸውም፥ ስለ አባታቸውና ስለ እናታቸውም የመጽናናት ጽዋ አያጠጡአቸውም። |
ወንድሞቹና እኅቶቹ ቀድሞም ያውቁት የነበሩት ሁሉ የሆነውን ሁሉ በሰሙ ጊዜ ወደ እርሱ መጡ፥ በቤቱም ከእርሱ ጋር እንጀራ በሉ፥ ጠጡም፤ አጽናኑትም፤ እግዚአብሔርም ባመጣበት ክፉ ነገር ሁሉ አደነቁ፤ እያንዳንዳቸውም ጥማድ በሬ፥ አራት ድራህማ የሚመዝን ወርቅና ብር ሰጡት።
እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሓይ በታችም የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፤ እነሆም፥ የተገፉት ሰዎች እንባ ነበረ፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፤ በሚገፉአቸውም እጅ ኀይል ነበረ። እነርሱን ግን የሚያጽናናቸው አልነበረም።
ከእንግዲህ ወዲህ አይመለስምና፥ የተወለደባትንም ሀገር አያይምና ለሚወጣ እጅግ አልቅሱ እንጂ ለሞተ አታልቅሱ፤ አትዘኑለትም።
ጤት። ግዳጅዋ ከእግርዋ በታች ነበረ፤ ፍጻሜዋን አላሰበችም፤ ከባድ ሸክምን ተሸከመች፤ የሚያጽናናትም የለም፤ አቤቱ! ጠላት ከፍ ከፍ ብሎአልና መከራዬን ተመልከት።
በቀስታ ተክዝ፤ ነገር ግን የሙታንን ልቅሶ አታልቅስ፤ መጠምጠሚያህን በራስህ ላይ አድርግ፤ ጫማህንም በእግርህ አጥልቅ፤ ከንፈሮችህንም አትሸፍን፤ የዕዝን እንጀራንም አትብላ።”
ለእግዚአብሔርም የወይን ጠጅን ቍርባን አያቀርቡም፤ መሥዋዕታቸውም ደስ አያሰኘውም፤ እንደ ኀዘንም እንጀራ ይሆንባቸዋል፤ የሚበላውም ሁሉ ይረክሳል፤ እንጀራቸውም ለሰውነታቸው ይሆናል እንጂ ወደ እግዚአብሔር ቤት አይገባም።
በኀዘኔም ጊዜ እኔ ከእርሱ አልበላሁም፤ ለርኩስም ነገር ከእርሱ የኀጢአት መሥዋዕት አልሠዋሁም፤ ከእርሱም አንዳች ለሞተ ሰው አልሰጠሁም፤ የአምላኬንም የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቼአለሁ፤ ያዘዝኸኝንም ሁሉ አድርጌአለሁ።