ኤርምያስ 15:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውኑ ብረትን፥ የሰሜንን ብረት፥ ናስንም የሚሰብር አለን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሰው ብረትን፣ ከሰሜን የመጣን ብረት፣ ንሓስንስ መስበር ይችላልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ ብረትን፥ የሰሜንን ብረት፥ ናስንም የሚሰብር አለን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! ከነሐስ ጋር የተቀላቀለን ብረት ለመስበር እንደማትችሉ ሁሉ በሰሜን በኩል ከጠላት የተቃጣውን አደጋ ልታሸንፉ አትችሉም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ብረትን፥ የሰሜንን ብረት፥ ናስንም የሚሰብር አለን? |
“እንደ ሸክላ ሠሪ ሥራ ውብ አድርጌ ሠራሁህ፤ ምድርን የሚያርስ ሁልጊዜ ያርሳልን? ጭቃ ሠሪውን፦ ምን ትሠራለህ? እጅ የለህምና መሥራት አትችልም ይለዋልን? ጭቃ ሠሪውን ይከራከረዋልን?
የእስራኤልም አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር ይገዙለት ዘንድ የብረትን ቀንበር በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ አንገት ላይ አድርጌአለሁ፤ እነርሱም ይገዙለታል፤ የምድረ በዳ አራዊትን ደግሞ ሰጥቼዋለሁ።”