ኤርምያስ 10:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንኳኔም ተበዘበዘ፤ አውታሬም ሁሉ ተቈረጠ፤ ልጆችና በጎችም የሉም ከእንግዲህ ወዲህ ለድንኳኔም ቦታ የለም ለመንጎችም መሰማሪያ የለም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድንኳኔ ፈርሷል፤ ገመዶቹም ሁሉ ተበጣጥሰዋል፤ ልጆቼ ጥለውኝ ሄደዋል፤ ከእንግዲህም አይመለሱም፤ ድንኳኔን ለመትከል፣ መጋረጃዬንም ለመዘርጋት ማንም የቀረ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንኳኔ ተበዘበዘ አውታሬም ሁሉ ተቈረጠ፤ ልጆቼም ከእኔ ወጥተው አይገኙም፤ ድንኳኔንም ከእንግዲህ ወዲህ የሚዘረጋ መጋረጃዎችንም የሚያነሣ የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድንኳኖቻችን ፈራረሱ፤ መወጠሪያ ገመዶችም ተቈራረጡ፤ ልጆቻችን በሙሉ ተሰደው ስለ ሄዱ፥ ድንኳኖቻችንን መልሶ የሚተክልልንና መጋረጃዎቻችንን የሚሰቅልልን አንድ እንኳ አልቀረም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንኳኔ ተበዘበዘ አውታሬም ሁሉ ተቈረጠ፥ ልጆቼም ከእኔ ወጥተው አይገኙም፥ ድንኳኔንም ከእንግዲህ ወዲህ የሚዘረጋ መጋረጃዎችንም የሚያነሣ የለም። |
ቃሌን በአፍሽ አደርጋለሁ፤ ሰማይን በዘረጋሁበትና ምድርን በመሠረትሁበት በእጄ ጥላ እጋርድሻለሁ፤ ጽዮንንም አንቺ ሕዝቤ ነሽ እላታለሁ።
የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ፤ መጋረጃዎችሽንም ዘርጊ፤ አትቈጥቢ፤ አውታሮችሽን አስረዝሚ፤ ካስሞችሽንም ትከዪ።
እኔ ከክፉ ቍስልሽ እፈውስሻለሁ፤ ጤናሽን እመልስልሻለሁ፤ ቍስልሽንም እፈውሳለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ማንም የማይሻት፥ የተጣለች ጽዮን ብለው ጠርተውሻልና።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የኀዘን፥ የልቅሶና የጩኸት ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች።
ሄ። ስለ ኀጢአቷ ብዛት እግዚአብሔር አዋርዶአታልና የሚዘባበቱባት በራስዋ ላይ ሆኑ፤ ጠላቶችዋም ተደሰቱ፤ ሕፃናቶችዋም በአስጨናቂዎች ፊት ተማርከዋል።