እነሆ በሜዳ ላይ ባለው ድንጋያማ ሸለቆ የምትቀመጥ ሆይ! እኔ በአንተ ላይ ነኝ፤ እናንተም፦ የሚያስደነግጠን ወይም ወደ መኖሪያችን የሚገባ ማን ነው? የምትሉ ሆይ! እኔ በእናንተ ላይ ነኝ፤
ኤርምያስ 10:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምሽግ ውስጥ የተቀመጥሽ ሆይ! ኀይልሽን ከውጭ ሰብስቢ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንቺ የተከበብሽ፤ ከያለበት ንብረትሽን ሰብስቢ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምሽግ ውስጥ የተቀመጥሽ ሆይ! ዕቃሽን ከመሬት ሰብስቢ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ በተከበበችው በኢየሩሳሌም ከተማ የምትኖሩ ሕዝብ ሆይ! ከዚያ ለመውጣት ንብረታችሁን በፍጥነት ሰብስቡ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምሽግ ውስጥ የተቀመጥሽ ሆይ፥ ዕቃሽን ከመሬት ሰብስቢ፥ |
እነሆ በሜዳ ላይ ባለው ድንጋያማ ሸለቆ የምትቀመጥ ሆይ! እኔ በአንተ ላይ ነኝ፤ እናንተም፦ የሚያስደነግጠን ወይም ወደ መኖሪያችን የሚገባ ማን ነው? የምትሉ ሆይ! እኔ በእናንተ ላይ ነኝ፤
እናንተ የብንያም ልጆች፥ ክፉ ነገር፥ ታላቅም ጥፋት ከመስዕ ይጐበኛልና ከኢየሩሳሌም ውስጥ ለመሸሽ ጽኑ፤ በቴቁሔ መለከቱን ንፉ፤ በቤትካሪም ላይ ምልክትን አንሡ።
በሀገርህ ሁሉ ያሉ፥ ትታመንባቸው የነበሩ፥ የረዘሙ፥ የጸኑም ቅጥሮች እስኪፈርሱ ድረስ፥ በከተሞችህ ሁሉ ያጠፋሃል፤ አምላክህም እግዚአብሔር በሰጠህ ምድር ሁሉ፥ በደጆች ሁሉ ያስጨንቅሃል።