La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 1:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም ዘመን፥ እስከ ይሁዳ ንጉሥ እስከ ኢዮ​ስ​ያስ ልጅ እስከ ሴዴ​ቅ​ያስ እስከ ዐሥራ አን​ደ​ኛው ዓመት ፍጻሜ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እስከ ተማ​ረ​ከ​ች​በት እስከ አም​ስ​ተ​ኛው ወር ድረስ መጣ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ደግሞም በይሁዳ ንጉሥ፣ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ንግሠ ዘመን፤ እንዲሁም በይሁዳ ንጉሥ፣ በኢዮስያስ ልጅ በሴዴቅያስ ንግሠ ዘመን፤ እስከ ዐሥራ አንደኛው ዓመት መጨረሻ ድረስ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ተማርኮ እስከ ሄደበት እስከ ዐምስተኛው ወር ድረስ ወደ እርሱ ይመጣ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በይሁዳም ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን፥ እስከ ይሁዳ ንጉሥ እስከ ኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ ዐሥራ አንደኛው ዓመት ፍጻሜ፥ ኢየሩሳሌም እስከ ተማረከችበት እስከ አምስተኛው ወር ድረስ መጣ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንዲሁም የኢዮስያስ ልጅ ኢዮአቄም በነገሠበት ዘመንና፥ ከዚያም በኋላ የኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ ነግሦ ዐሥራ አንድ ዓመት እስከሆነው ድረስ ማለት በዚያው ዓመት በአምስተኛው ወር የኢየሩሳሌም ሕዝብ ተማርኮ እስከ ተወሰደ ድረስ የእግዚአብሔር ቃል በኤርምያስ አማካይነት ተነግሮአል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በይሁዳም ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን፥ እስከ ይሁዳ ንጉሥ እስከ ኢዮስያስ ልጅ እስከ ሴዴቅያስ እስከ አሥራ አንደኛው ዓመት ፍጻሜ፥ ኢየሩሳሌም እስከ ተማረከችበት እስከ አምስተኛው ወር ድረስ መጣ።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 1:3
19 Referencias Cruzadas  

ፈር​ዖን ኒካ​ዑም የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ስ​ያ​ስን ልጅ ኤል​ያ​ቄ​ምን በአ​ባቱ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ፋንታ አነ​ገሠ፤ ስሙ​ንም ኢዮ​አ​ቄም ብሎ ለወ​ጠው። ዮአ​ክ​ስ​ንም ወስዶ ወደ ግብፅ አፈ​ለ​ሰው፤ በዚ​ያም ሞተ።


የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ የዮ​አ​ኪ​ንን አጎት ማታ​ን​ያን በእ​ርሱ ፋንታ አነ​ገሠ፤ ስሙ​ንም ሴዴ​ቅ​ያስ ብሎ ለወ​ጠው።


የኢ​ዮ​ስ​ያ​ስም ልጆች፤ በኵሩ ዮሐ​ናን፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ኢዮ​አ​ቄም፥ ሦስ​ተ​ኛ​ውም ሴዴ​ቅ​ያስ፥ አራ​ተ​ኛ​ውም ሰሎም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርና ሠራ​ዊቱ ሁሉ፥ ከእ​ጁም ግዛት በታች ያሉ የም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ፥ አሕ​ዛ​ብም ሁሉ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንና የይ​ሁ​ዳን ከተ​ሞች ሁሉ ይወጉ በነ​በረ ጊዜ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦


በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም ዘመን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፤ እን​ዲህ ሲል፦


“አንድ የመ​ጽ​ሐፍ ክር​ታስ ውሰድ፥ ለአ​ን​ተም ከተ​ና​ገ​ር​ሁ​በት ቀን ከይ​ሁዳ ንጉሥ ከኢ​ዮ​ስ​ያስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ላይ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ህን ቃል ሁሉ ጻፍ​በት።


በሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስም በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በአ​ራ​ተ​ኛው ወር፥ ከወ​ሩም በዘ​ጠ​ነ​ኛው ቀን ከተ​ማ​ዪቱ ተለ​ያ​የች።


ለምድሩ ሕዝብ ሁሉ ለካህናትም እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ በዚህ በሰባው ዓመት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር በጾማችሁና ባለቀሳችሁ ጊዜ፥ በውኑ ለእኔ ጾም ጾማችሁልኝ?


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአሥረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሐሤትም በዓላት ይሆናል፣ ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ውደዱ።