ያዕቆብ 5:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሀብታችሁ ተበላሽቶአል፤ ልብሳችሁም በብል ተበልቶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሀብታችሁ ሻግቷል፤ ልብሳችሁንም ብል በልቶታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሀብታችሁ ተበላሽቶአል፤ ልብሳችሁም በብል ተበልቶአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሀብታችሁ ሁሉ በስብሶአል። ልብሳችሁንም ብል በልቶታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሀብታችሁ ተበላሽቶአል፥ ልብሳችሁም በብል ተበልቶአል። |
እንደ ልብስ ፈጥነው ያረጃሉና አይቈዩም፤ ብል እንደ በላውም ይሆናሉ፤ ጽድቄ ግን ለዘለዓለም፥ ማዳኔም ለልጅ ልጅ ይሆናል።
ቆቅ ጮኸች፤ ያልወለደችውንም ዐቀፈች፤ በዐመፅ ባለጠግነትን የሚሰበስብ ሰውም እንደዚሁ ነው፤ በእኩሌታ ዘመኑ ይተወዋል፤ በፍጻሜውም ሰነፍ ይሆናል።
ሀብታችሁን ሸጣችሁ ምጽዋት ስጡ፤ ሌባ በማያገኝበት ነቀዝም በማያበላሽበት፥ የማያረጅ ከረጢት፥ የማያልቅም መዝገብ በሰማያት ለእናንተ አድርጉ።