ያዕቆብ 4:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕግን የሚሰጥና የሚፈርድ አንድ ነው፤ እርሱም ሊያድን ሊያጠፋም የሚችል ነው፤ በሌላው ግን የምትፈርድ አንተ ማን ነህ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕግን የሚሰጥና የሚፈርድ አንድ ብቻ ነው፤ እርሱም ሊያድንና ሊያጠፋ የሚችል ነው፤ ነገር ግን በባልንጀራህ ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕግን የሚሰጥና የሚፈርድ አንድ ብቻ ነው፤ እርሱም ሊያድንና ሊያጠፋ የሚችል ነው፤ ነገር ግን በባልንጀራህ ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕግን የሚሰጥና የሚፈርድ አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ ሊያድንም ሊያጠፋም የሚችል እርሱ ብቻ ነው፤ ታዲያ፥ በሰው ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕግን የሚሰጥና የሚፈርድ አንድ ነው፤ እርሱም ሊያድን ሊያጠፋም የሚችል ነው፤ በሌላው ግን የምትፈርድ አንተ ማን ነህ? |
አምላካችን እግዚአብሔር ታላቅ ነውና ቸል አይለንም፤ እግዚአብሔር ፈራጃችን ነው፤ እግዚአብሔር አምላካችን ነው። እግዚአብሔር ንጉሣችን ነው፤ እርሱ እግዚአብሔር ያድነናል።
ነገር ግን፤ የምትፈሩትን አሳያችኋለሁ፤ እናንተስ ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም ሊጥል ሥልጣን ያለውን ፍሩት፤ አዎ፥ እላችኋለሁ፤ እርሱን ፍሩ።
እንግዲህ ከዛሬ ጀምሮ እርስ በርሳችን አንነቃቀፍ፤ ይልቁንም ለወንድም እንቅፋትን ወይም ማሰናከያን ማንም እንዳያኖር ይህን ዐስቡ።
እንግዲህ የሌላውን ሎሌ የምትነቅፍ አንተ ማነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለጌታው ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር ሊያነሣው ይችላልና ይቆማል።
አንተ ሰው ሆይ፥ እውነት ለሚፈርደው ለእግዚአብሔር ምን ትመልስለታለህ? በወንድምህ ላይ የምትጠላውን ያን ሥራ አንተ ራስህ ከሠራኸው በራስህ የምትፈርድ አይደለምን? አንተ ራስህ ያን ሥራ ትሠራዋለህና።
ዘወትር በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡትን ሊያድናቸው ይቻለዋል፤ ለዘለዓለምም ሕያው ነውና ያስታርቃቸዋል።
ናባልም ተነሥቶ ለዳዊት ብላቴኖች መለሰላቸው እንዲህም አላቸው፥ “ዳዊት ማን ነው? የእሴይስ ልጅ ማን ነው? እያንዳንዳቸው ከጌቶቻቸው የኰበለሉ አገልጋዮች ዛሬ ብዙ ናቸው።