ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ፤ እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቆአልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ፊት ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል።
ያዕቆብ 3:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ሥራ ሁሉ አሉና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቅናትና ራስ ወዳድነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ሥራ ሁሉ ይገኛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቅናትና ራስ ወዳድነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ሥራ ሁሉ ይኖራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቅናትና ራስ ወዳድነት ባሉበት ስፍራ ሁከትና ክፉ ሥራ ሁሉ ይኖራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና። |
ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ፤ እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቆአልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ፊት ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል።
አውናንም ዘሩ ለእርሱ እንዳይሆን ዐወቀ፤ ወደ ወንድሙ ሚስትም በገባ ጊዜ ለወንድሙ ዘር እንዳይተካ ዘሩን በምድር ያፈስሰው ነበር።
ከተማውም ሁሉ ታወከ፤ የመቄዶንያን ሰዎች የጳውሎስን ወዳጆች ጋይዮስንና አርስጥሮኮስንም ከእነርሱ ጋር እየጐተቱበአንድነት ወደ ጨዋታው ቦታ ሮጡ።
በሥጋዊ ሕግም ትኖራላችሁና እርስ በርሳችሁ የምትቃኑና የምትከራከሩ ከሆነ ግን ሥጋውያን መሆናችሁ አይደለምን? እንደ ሰው ልማድስ የምትኖሩ መሆናችሁ አይደለምን?
ነገር ግን ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ እንደምወደው ሆናችሁ ያላገኘኋችሁ እንደ ሆነ፤ እኔም እንደማትወዱት እሆንባችኋለሁ ብዬ እፈራለሁ፤ ወይም እኮ በመካከላችሁ ክርክር፥ ኵራት፥ መቀናናት፥ መበሳጨት፥ መዘባበት፥ ወይም መተማማት፥ መታወክ፥ ወይም ልብን ማስታበይ ይኖር ይሆናል።
ጣዖት ማምለክ፥ ሥራይ ማድረግ፥ መጣላት፥ ኵራት፥ የምንዝር ጌጥ፥ ቅናት፥ ቍጣ፥ ጥርጥር፥ ፉክክር፥ ምቀኝነት፥ መጋደል፥ ስካር ይህንም የመሰለ ሁሉ ነው።
ከክፉው እንደ ነበረ ወንድሙንም እንደ ገደለ እንደ ቃየል አይደለም፤ ስለ ምንስ ገደለው? የገዛ ሥራው ክፉ፥ የወንድሙም ሥራ ጽድቅ ስለ ነበረ ነው።