እርጎና መዓር፥ ያን ያዘጋጀውንም ጥጃ አመጣ፤ በፊታቸውም አቀረበው፤ እርሱም ከዛፉ በታች በፊታቸው ቆሞ ያሳልፍላቸው ነበር፤ እነርሱም በሉ።
ኢሳይያስ 7:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወተትም ይበዛል፤ በሀገሪቱ መካከል የቀረ ሁሉ ቅቤና ማር ይበላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሚሰጡትም የተትረፈረፈ ወተት ቅቤ ይበላል፤ በምድሪቱም የቀሩ ሁሉ ቅቤና ማር ይበላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሚሰጡትም የተትረፈረፈ ወተት ቅቤ ይበላል፤ በምድሪቱም የቀሩ ሁሉ ቅቤና ማር ይበላሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ከሚሰጡት ብዙ ወተት የሚያስፈልገውን ምግብ ሁሉ ያገኛል፤ ከዚህም የተነሣ በምድሪቱ ላይ የሚተርፉ ሰዎች ምግባቸው ማርና ወተት ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሚሠጡት ወተት ብዛት የተነሣ ቅቤ ይበላል፥ በአገሪቱም መካከል የቀረ ሁሉ ቅቤና ማር ይበላል። |
እርጎና መዓር፥ ያን ያዘጋጀውንም ጥጃ አመጣ፤ በፊታቸውም አቀረበው፤ እርሱም ከዛፉ በታች በፊታቸው ቆሞ ያሳልፍላቸው ነበር፤ እነርሱም በሉ።
ማርና ቅቤ፥ በግና ላም ይበሉ ዘንድ ለዳዊትና ከእርሱ ጋር ላሉ ሰዎች አመጡ። ሕዝቡ በምድረ በዳ ተርበውና ተጠምተው ደክመው ነበርና።
ድሆችም በውስጣችሁ ይሰማራሉ፤ ድሆች ሰዎችም በሰላም ያርፋሉ፤ ዘራችሁንም ረኃብ ያጠፋቸዋል፤ ከእናንተም የቀሩት ያልቃሉ።