በእጃችሁ ሥራ ሁሉ ታስቈጡኝ ዘንድ ትታችሁኛልና፥ ለሌሎች አማልክትም ዐጥናችኋልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነድዳል፥ አይጠፋምም።
ኢሳይያስ 65:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኒህ ሕዝብ ዘወትር የሚያስቈጡኝ ናቸው፤ እነርሱ በአትክልት ውስጥ የሚሠዉ በጡብም ላይ ለአጋንንት የሚያጥኑ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአትክልት ቦታዎች መሥዋዕት የሚያቀርቡ፣ በሸክላ መሠዊያዎች ላይ ዕጣን የሚያጥኑ፣ ዘወትር በፊቴ የሚያስቈጡኝ ሕዝብ ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ ሕዝብ ዘወትር በፊቴ ቁጣን ይቀሰቅሳሉ፥ እነርሱ በአትክልት ውስጥ የሚሠዉ፥ በጡብም ላይ የሚያጥኑ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህም ሰዎች በአትክልት ቦታ ውስጥ መሥዋዕት በመሠዋትና በጡብ ላይ በፊቴ ሁልጊዜ ዕጣን በማጠን እኔን የሚያስቈጡኝ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ ሕዝብ ዘወትር የሚያስቈጡኝ ናቸው፥ እነርሱ በአትክልት ውስጥ የሚሠዉ በጡብም ላይ የምያጥኑ፥ |
በእጃችሁ ሥራ ሁሉ ታስቈጡኝ ዘንድ ትታችሁኛልና፥ ለሌሎች አማልክትም ዐጥናችኋልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነድዳል፥ አይጠፋምም።
ኢየሩሳሌም ተፈትታለችና፥ ይሁዳም ወድቃለችና፥ አንደበታቸውም ዐመፅን ስለሚናገር ለእግዚአብሔር አልታዘዙም።
“በአትክልት ቦታ ውስጥ ሰውነታቸውን የሚያጠሩና የሚያነጹ፥ በምግብ ቦታም የእሪያን ሥጋ፥ አስጸያፊ ነገርንም አይጥንም የሚበሉ በአንድነት ይጠፋሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።
በሬን የሚሠዋልኝ ኃጥእ ውሻን እንደሚያርድልኝ ነው፤ የእህልን ቍርባን የሚያቀርብም የእሪያን ደም እንደሚያቀርብ ነው፤ ዕጣንንም ለመታሰቢያ የሚያጥን አምላክን እንደሚፀርፍ ነው፤ እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ፤ ነፍሳቸውም በርኵሰታቸው ደስ ይላታል።
እግዚአብሔርም በንጉሡ በኢዮስያስ ዘመን እንዲህ አለኝ፥ “ከዳተኛዪቱ እስራኤል ያደረገችውን አየህን? ወደ ረዘመው ተራራ ሁሉ፥ ወደ ለመለመ ዛፍም ሁሉ በታች ሄደች፤ በዚያም አመነዘረች።
እሰጣቸውም ዘንድ እጄን ወደ አነሣሁላቸው ምድር አገባኋቸው፤ ከፍ ያለውን ኮረብታ ሁሉ፥ ቅጠላማውንም ዛፍ ሁሉ አዩ፤ በዚያም ለጣዖቶቻቸው መሥዋዕታቸውን ሠዉ፤ በዚያም የሚያስቈጣኝን፤ ቍርባናቸውን አቀረቡ፤ በዚያም ደግሞ ጣፋጩን ሽታቸውን አደረጉ፤ በዚያም የመጠጥ ቍርባናቸውን አፈሰሱ።
ስለዚህ የእስራኤል ልጆች በሜዳ የሚያርዱትን መሥዋዕታቸውን ወደ እግዚአብሔር ወደ ምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ያመጡታል፤ ወደ ካህኑም አምጥተው ለእግዚአብሔር ለድኅነት መሥዋዕት ይሠዉታል።
አምላክ ባልሆነው አስቀኑኝ፤ በጣዖቶቻቸውም አስቈጡኝ፤ እኔም ሕዝብ ባልሆነው አስቀናቸዋለሁ፤ በማያስተውል ሕዝብም አስቈጣቸዋለሁ።