እንደዚህ በልቡ ያሰበውን መናገሩን ሳይፈጽም እንዲህ ሆነ፦ የአብርሃም ወንድም የናኮር ሚስት የሚልካ ልጅ የባቱኤል ሴት ልጅ ርብቃ እነሆ፥ መጣች፥ እንስራዋንም በጫንቃዋ ተሸክማ ነበር።
ኢሳይያስ 65:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እንዲህም ይሆናል፤ ሳይጠሩ እመልስላቸዋለሁ፤ ገናም ሲናገሩ እነሆ፥ አለሁ እላቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገና ሳይጣሩ እመልስላቸዋለሁ፤ ተናግረው ሳይጨርሱ እሰማለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ይሆናል፤ ሳይጠሩ እመልስላቸዋለሁ፥ ገናም ሲናገሩ እሰማለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔን በልመና ከመጥራታቸው በፊት እመልስላቸዋለሁ፤ እየጸለዩም ሳለ እሰማቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ይሆናል፥ ሳይጠሩ እመልስላቸዋለሁ፥ ገናም ሲናገሩ እሰማለሁ። |
እንደዚህ በልቡ ያሰበውን መናገሩን ሳይፈጽም እንዲህ ሆነ፦ የአብርሃም ወንድም የናኮር ሚስት የሚልካ ልጅ የባቱኤል ሴት ልጅ ርብቃ እነሆ፥ መጣች፥ እንስራዋንም በጫንቃዋ ተሸክማ ነበር።
የአሞጽም ልጅ ኢሳይያስ እንዲህ ብሎ ወደ ሕዝቅያስ ላከ፥ “የሠራዊት ጌታ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለ አሦር ንጉሥ ስለ ሰናክሬም ወደ እኔ የለመንኸውን ሰምቻለሁ።
ቅዱስ ሕዝብ በኢየሩሳሌም ውስጥ በጽዮን ይኖራል፤ ልቅሶን አልቅሺ፤ ይቅር በለኝም በዪ፤ ልቅሶሽን ባየ ጊዜ ይቅር ይልሻል፤ ሰምቶሻልና።
ድሆችና ምስኪኖች ውኃ ይሻሉ፤ አያገኙምም፤ ምላሳቸውም በጥማት ደርቋል፤ እኔ ጌታ እግዚአብሔር እሰማቸዋለሁ፤ የእስራኤል አምላክ እኔ አልተዋቸውም።
ያን ጊዜ ትጠራለህ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ፤ እርሱም፦ እነሆኝ፥ ይልሃል። የዐመፅ እስራትን ከመካከልህ ብታርቅ፥ ጣትህንም መጥቀስ ማንጐራጐርንም ብትተው፥
ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።
ሲጸልዩም በአንድነት ተሰብስበው የነበሩበት ቦታ ተናወጠ፤ በሁሉም ላይ መንፈስ ቅዱስ መላባቸውና የእግዚአብሔርን ቃል በግልጥ አስተማሩ።