ኢሳይያስ 52:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙዎች አሕዛብ እርሱን ያደንቃሉ፤ ነገሥታትም አፋቸውን ይዘጋሉ፤ ስለ እርሱ ያልተወራላቸው ያውቁታልና፥ ያልሰሙትም ያስተውሉታልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ብዙ መንግሥታትን ያስደንቃል፤ በርሱ ምክንያት ነገሥታት አፋቸውን ይይዛሉ፤ ያልተነገራቸውን ያያሉ፤ ያልሰሙትንም ያስተውላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያልተነገረላቸውን ያያሉና፥ ያልሰሙትንም ያስተውላሉና ነገሥታት ስለ እርሱ አፋቸውን ይዘጋሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀድሞ ያልተነገራቸውን ነገር ስለሚያዩና ያልሰሙትን ነገር ስለሚያስተውሉ ብዙ ሕዝቦች ስለ አገልጋዬ ይደነቃሉ፤ ነገሥታትም በእርሱ በመደነቅ የሚናገሩትን ያጣሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያልተነገረላቸውን ያያሉና፥ ያልሰሙትንም ያስተውላሉና ነገሥታት ስለ እርሱ አፋቸውን ይዘጋሉ። |
“አንተ ስታስተምረኝ እኔ የምመልሰው ምን አለኝ? ይህንስ እየሰማሁ ከእግዚአብሔር ጋር እከራከር ዘንድ እኔ ምንድን ነኝ? እጄን በአፌ ላይ ከማኖር በቀር የምመልሰው ምንድን ነው?
ነገሥታትም አሳዳጊዎች አባቶችሽ ይሆናሉ፤ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፤ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ፤ እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ አያፍሩም።”
ታዳጊህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሕይወቱን የሚያስጨንቃትን፥ በአሕዛብ የተጠላውን የአለቆችን ባርያ ቀድሱት፤ ነገሥታት ያዩታል፤ አለቆችም ስለ እግዚአብሔር ብለው ተነሥተው ይሰግዱለታል፤ የእስራኤል ቅዱስ ታማኝ ነውና፥ እኔም መርጨሃለሁና።”
ጽድቄ ፈጥና ትመጣለች፤ ማዳኔም እንደ ብርሃን ትደርሳለች፤ አሕዛብ በክንዴ ይታመናሉ፤ ደሴቶች እኔን ተስፋ ያደርጋሉ፤ በክንዴም ይታመናሉ።
እነሆ፥ የማያውቁህ ሕዝብ ይጠሩሃል፤ የእስራኤል ቅዱስ አክብሮሃልና ስለ አምላክህ ስለ እግዚአብሔር የማያውቁህ ሕዝብ በአንተ ይማጠናሉ።
ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ፤ እናንተም ከርኵሰታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ፤ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አነጻችኋለሁ።
ንጹሕም ሰው ሂሶጱን ወስዶ በውኃው ውስጥ ያጠልቀዋል፤ በቤቱም፥ በዕቃውም ሁሉ፥ በዚያም ባሉ ሰዎች ላይ፥ አጥንቱንም ወይም የተገደለውን፥ ወይም የሞተውን፥ ወይም መቃብሩን በነካው ላይ ይረጨዋል።
ታነጻቸው ዘንድ እንዲህ ታደርግላቸዋለህ፤ በማንጻት ውኃ ትረጫቸዋለህ፤ ሰውነታቸውን ሁሉ ይላጩ፤ ልብሳቸውንም ይጠቡ፤ ንጹሓንም ይሆናሉ።
እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም፥ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”
አሁን ግን በእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ ብሎና የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ ከአብ ገንዘብ አድርጎ ይህን ዛሬ የምታዩትንና የምትሰሙትን አፈሰሰው።
እንግዲህ ከክፉ ሕሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተን፥ ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ።
የአዲስ ኪዳንም መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ ተረጨው ደሙ ደርሳችኋል።