| ኢሳይያስ 55:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 እነሆ፥ የማያውቁህ ሕዝብ ይጠሩሃል፤ የእስራኤል ቅዱስ አክብሮሃልና ስለ አምላክህ ስለ እግዚአብሔር የማያውቁህ ሕዝብ በአንተ ይማጠናሉ።Ver Capítulo አዲሱ መደበኛ ትርጒም5 እነሆ፤ የማታውቃቸውን መንግሥታት ትጠራለህ፤ የማያወቁህ መንግሥታት በፍጥነት ወደ አንተ ይመጣሉ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር አምላክህ፣ የእስራኤል ቅዱስ፣ በክብሩ ከፍ ከፍ አድርጎሃል።”Ver Capítulo መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 እነሆ፥ የማታውቀውን ሕዝብ ትጠራለህ፥ የእስራኤልም ቅዱስ አክብሮሃልና ስለ አምላክህ ስለ ጌታ የማያውቅህ ሕዝብ ወደ አንተ ይሮጣል።Ver Capítulo አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 እኔ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር አምላክህ ስላከበርኩህ እነሆ፥ የማታውቃቸውን ሕዝቦች ትጠራለህ፤ የማያውቁህም ሕዝቦች ወደ አንተ ይፈጥናሉ።”Ver Capítulo መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 እነሆ፥ የማታውቀውን ሕዝብ ትጠራለህ፥ የእስራኤልም ቅዱስ አክብሮሃልና ስለ አምላክህ ስለ እግዚአብሔር የማያውቁህ ሕዝብ ወደ አንተ ይሮጣሉ።Ver Capítulo |