ኢሳይያስ 49:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ እጄን ወደ አሕዛብ አነሣለሁ፤ ዓርማዬንም ወደ ደሴቶች አቆማለሁ፤ ወንዶች ልጆችሽንም በብብታቸው ታቅፈው ያመጡአቸዋል፤ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃቸው ላይ ይሸከሙአቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ አሕዛብን በጥቅሻ እጣራለሁ፤ ዐርማዬንም ለሕዝቦች ከፍ አደርጋለሁ፤ ወንዶች ልጆችሽን በዕቅፋቸው ያመጡልሻል፤ ሴቶች ልጆችሽንም በትከሻቸው ይሸከሙልሻል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እጄን ወደ አሕዛብ አነሣለሁ፥ ዓላማዬንም ወደ ወገኖች አቆማለሁ፤ ወንዶች ልጆችሽንም በዕቅፋቸው ያመጡአቸዋል፥ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃቸው ላይ ይሸከሙአቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ወንዶች ልጆችሽን በክንዳቸው፥ ሴቶች ልጆችሽንም በትከሻቸው ተሸክመው ያመጡ ዘንድ ለመንግሥታት ምልክት እሰጣለሁ፤ ለሕዝቦችም ዐርማን አነሣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እጄን ወደ አሕዛብ አነሣለሁ፥ ዓላማዬንም ወደ ወገኖች አቆማለሁ፥ ወንዶች ልጆችሽንም በብብታቸው ያመጡአቸዋል፥ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃቸው ላይ ይሸከሙአቸዋል። |
አሕዛብም ይዘው ወደ ስፍራቸው ያመጡአቸዋል፤ የእስራኤልም ወገኖች ይካፈሏቸዋል፤ በዚያም ሀገር ይበዛሉ፤ በዚያም ወንዶች ባሮችና ሴቶች ባሮች ይሆናሉ። ማርከው የወሰዷቸውም ለእነርሱ ምርኮኞች ይሆናሉ፤ የገዙአቸውም ይገዙላቸዋል።
በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፤ ከእነርሱም ከሞት የዳኑትን ዝናዬን ወዳልሰሙ፥ ክብሬንም ወዳላዩ ወደ አሕዛብ ወደ ተርሴስ፥ ወደ ፉጥ፥ ወደ ሉድ፥ ወደ ሞሳሕ፥ ወደ ቶቤል፥ ወደ ኤላድ በሩቅ ወዳሉ ደሴቶች እልካቸዋለሁ፤ በአሕዛብም መካከል ክብሬን ይናገራሉ።
የእስራኤል ልጆች ቍርባናቸውን በምስጋና ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደሚያመጡ፥ እንዲሁ ለእግዚአብሔር ቍርባን ይሆን ዘንድ ወንድሞቻችሁን ሁሉ፥ በፈረሶችና በሰረገሎች፥ በአልጋዎችና በበቅሎዎች፥ በጠያር ግመሎችም ላይ አድርገው፥ ከአሕዛብ ሁሉ ወደ ተቀደሰችው ከተማ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጡአቸዋል፥ ይላል እግዚአብሔር።
ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፣ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፣ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።