ሰነፍ በልቡ፥ “እግዚአብሔር የለም” ይላል። በሥራቸው ረከሱ፥ ጐሰቈሉም፤ በጎ ነገርን የሚሠራት የለም። አንድም እንኳ የለም።
ኢሳይያስ 49:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጽዮን ግን፥ “እግዚአብሔር ትቶኛል፤ ጌታም ረስቶኛል” አለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጽዮን ግን፣ “እግዚአብሔር ትቶኛል፤ ጌታም ረስቶኛል” አለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጽዮን ግን፦ “ጌታ ትቶኛል፥ እርሱ ረስቶኛል” አለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢየሩሳሌም ሕዝብ ግን፥ “እግዚአብሔር ትቶናል፤ ጌታዬም ረስቶናል” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጽዮን ግን፦ እግዚአብሔር ትቶኛል ጌታም ረስቶኛል አለች። |
ሰነፍ በልቡ፥ “እግዚአብሔር የለም” ይላል። በሥራቸው ረከሱ፥ ጐሰቈሉም፤ በጎ ነገርን የሚሠራት የለም። አንድም እንኳ የለም።
ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤልም ሆይ፥ መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች፤ አምላኬም ከእኔ ርቋል፤ ፍርዴንም ትትዋል፤ ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ?
እግዚአብሔር ሕዝቡን ይቅር ብሎአልና፥ ከሕዝቡም ችግረኞቹን አጽንቶአልና። ሰማያት ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ፤ ምድርም ደስ ይበላት፤ ተራሮችም እልል ይበሉ።
“በውኑ ሴት፥ ልጅዋን ትረሳለችን? ከማኅፀንዋ ለተወለደውስ አትራራምን? ሴት ይህን ብትረሳ፥ እኔ አንቺን አልረሳሽም።
እግዚአብሔር እንደ ተተወችና እንደ ተበሳጨች፥ በልጅነቷም እንደ ተጠላች ሴት የጠራሽ አይደለም፥ ይላል አምላክሽ።
ስለዚህ፥ እነሆ- ፈጽሜ እረሳችኋለሁ እናንተንም፥ ለእናንተና ለአባቶቻችሁም የሰጠኋትን ከተማ ከፊቴ አንሥቼ እጥላለሁ።
እግዚአብሔርም ከሩቅ ተገለጠልኝ፤ እንዲህም አለኝ፥ “በዘለዓለም ፍቅር ወድጄሃለሁ፤ ስለዚህ በቸርነት ሳብሁህ።
“አንተም የሰው ልጅ ሆይ! የእስራኤልን ቤት፦ እናንተ፦ በደላችንና ኀጢአታችን በላያችን አሉ፤ እኛም ሰልስለንባቸዋል፤ እንዴትስ በሕይወት እንኖራለን? ብላችሁ ተናግራችኋል በላቸው።