እናንተ የጌላቡሄ ተራሮች ሆይ፥ ዝናብና ጠል አይውረድባችሁ፤ ቍርባንንም የሚያበቅል እርሻ አይሁንባችሁ። የኀያላን ጋሻ በዚያ ወድቆአልና፤ የሳኦልም ጋሻ ዘይት አልተቀባምና።
ኢሳይያስ 43:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለቆች መቅደሴን አረከሱ፤ ስለዚህም ያዕቆብን ለጥፋት፥ እስራኤልንም ለውርደት ሰጠሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የመቅደስህን አለቆች አዋርዳለሁ፤ ያዕቆብን ለጥፋት፣ እስራኤልን ለስድብ እዳርጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ የመቅደሱን አለቆች አረከስኩ፥ ያዕቆብንም እርግማን፥ እስራኤልንም ስድብ አደረግሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የቤተ መቅደስን ሹማምንት ርኲሰት ገለጥኩ፤ የያዕቆብም ልጆች እስራኤላውያን እንዲዋረዱና ፈጽመውም እንዲጠፉ አደረግሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ የመቅደሱን አለቆች አረከስሁ፥ ያዕቆብንም እርግማን፥ እስራኤልንም ስድብ አደረግሁ። |
እናንተ የጌላቡሄ ተራሮች ሆይ፥ ዝናብና ጠል አይውረድባችሁ፤ ቍርባንንም የሚያበቅል እርሻ አይሁንባችሁ። የኀያላን ጋሻ በዚያ ወድቆአልና፤ የሳኦልም ጋሻ ዘይት አልተቀባምና።
ከአልዓዛርና ከኢታምርም ልጆች መካከል የንዋያተ ቅዱሳቱና የእግዚአብሔር ቤት አለቆች ነበሩና እነዚህና እነዚያ እንዲህ በዕጣ ተመደቡ።
ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ጐልማሶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ለንጉሣቸው ለሴዴቅያስም አልራራለትም፤ ደናግሉንም አልማረም፤ ሽማግሌዎቻቸውንም ወሰዳቸው፤ ሁሉንም እግዚአብሔር በእጁ አሳልፎ ሰጠው።
ስለዚህ ምድር ትውጣቸዋለች፤ በእርስዋ የተቀመጡ በድለዋልና፤ በምድር የሚኖሩ ሰዎችም ይቸገራሉ፤ ጥቂት ሰዎችም ይቀራሉ።
በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር፤ ርስቴንም አረከስሽ፤ በእጅሽም አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ ለሽማግሌዎቻቸው አልራራሽም፤ ቀንበራቸውንም እጅግ አክብደሻል።
ስማችሁንም እኔ ለመረጥኋቸው ሕዝቤ ጥጋብ አድርጋችሁ ትተዋላችሁ፤ ጌታ እግዚአብሔርም ያጠፋችኋል፤ ባሪያዎች ግን በሐዲስ ስም ይጠራሉ።
በማሳድዳቸውም ስፍራ ሁሉ ለስድብና ለምሳሌ፥ ለጥላቻና ለርግማን ይሆኑ ዘንድ በምድር መንግሥታት ሁሉ እንዲበተኑ አደርጋለሁ።
ቤት። እግዚአብሔር የያዕቆብን መልካም ነገር ሁሉ አሰጠመ፤ አልራራምም፤ በመዓቱ የይሁዳን ሴት ልጅ አንባዎች አፈረሰ፤ ወደ ምድርም አወረዳቸው፤ መንግሥቷንና ግዛቷንም አረከሰ።
ሬስ። ስለ እርሱ፥ “በአሕዛብ ውስጥ በጥላው በሕይወት እንኖራለን” ያልነው፥ በእግዚአብሔር የተቀባ፥ የሕይወታችን እስትንፋስ፥ በወጥመዳቸው ተያዘ።
በቍጣዬና በመቅሠፍቴ በተበቀልሁሽ ጊዜ በዙሪያሽ በአሉ በአሕዛብ ዘንድ ትጨነቂያለሽ፤ ትደነግጫለሽም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
እንዲህም አለኝ፦ ይህ በምድር ፊት ሁሉ ላይ የሚወጣው እርግማን ነው፣ የሚሰርቅ ሁሉ በእርሱ ላይ በዚህ በኩል እንደ ተጻፈው ሁሉ ይጠፋል፥ በሐሰት የሚምልም ሁሉ በእርሱ ላይ በዚያ በኩል እንደ ተጻፈው ሁሉ ይጠፋል።
የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በአሕዛብ ዘንድ እርግማን እንደ ነበራችሁ፥ እንዲሁ አድናችኋለሁ፥ በረከትም ትሆናላችሁ፣ አትፍሩ፥ እጃችሁንም አበርቱ።