አንተም፦ ‘በርግጥ መልካም አደርግልሃለሁ፥ ዘርህንም ከብዛቱ የተነሣ እንደማይቈጠር እንደ ባሕር አሸዋ አደርጋለሁ ብለህ ነበር።’ ”
ኢሳይያስ 43:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሳስበኝ፤ በአንድነትም ሆነን እንፋረድ፤ እንድትጸድቅ አስቀድመህ በደልህን ተናገር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስኪ ያለፈውን አስታውሰኝ፤ ተቀራርበን እንከራከርበት፤ ትክክለኛ ስለ መሆንህም አስረዳ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሳስበኝ፥ በአንድነትም ሆነን እንፋረድ፤ እንድትጸድቅ ነገርህን ተናገር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አስታውሱኝ፤ ጉዳያችሁን አቅርባችሁ ትክክለኛነታችሁን አስመስክሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሳስበኝ፥ በአንድነትም ሆነን እንፋረድ፥ እንድትጸድቅ ነገርህን ተናገር። |
አንተም፦ ‘በርግጥ መልካም አደርግልሃለሁ፥ ዘርህንም ከብዛቱ የተነሣ እንደማይቈጠር እንደ ባሕር አሸዋ አደርጋለሁ ብለህ ነበር።’ ”
“ኑና እንዋቀስ” ይላል እግዚአብሔር፤ ኀጢአታችሁ እንደ አለላ ቢሆን እንደ በረዶ አነጻዋለሁ፤ እንደ ደምም ቢቀላ እንደ ባዘቶ አጠራዋለሁ።
አሕዛብ ሁሉ በአንድነት ተሰበሰቡ፤ አለቆችም ተከማቹ፤ ይህን ማን ይናገራል? የቀድሞውንስ ማን ይነግራችኋል? ይጸድቁ ዘንድ ምስክሮቻቸውን ያምጡ፤ ሰምተውም፦ እውነትን ይናገሩ።
የሚያጸድቀኝ ቅርብ ነው፤ ከእኔስ ጋር የሚከራከር ማን ነው? እስቲ በእኔ ላይ ይነሣ፤ የሚከራከረኝስ ማን ነው? ወደ እኔ ይቅረብ።
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለዚህ ደግሞ አደርግላቸው ዘንድ የእስራኤል ቤት ይሹኛል፤ ሰውንም እንደ መንጋ አበዛላቸዋለሁ።
እርሱም፥ “እናንተስ ለሰው ይምሰል ትመጻደቃላችሁ፤ እግዚአብሔርም ልቡናችሁን ያውቃል፤ በሰው ዘንድ የከበረ በእግዚአብሔር ዘንድ የተናቀ ይሆናልና።
የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያውቁአትምና በራሳቸውም ጽድቅ ጸንተው ሊኖሩ ወደዱ፤ ለእግዚአብሔር ጽድቅ ግን መገዛት ተሳናቸው።