ኢሳይያስ 40:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አለቆችንም የሚገዛላቸው እንዳይኖር የሚያደርግ ምድርንም እንደ ኢምንት የሚያደርጋት እርሱ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አለቆችን ኢምንት፣ የዚህን ዓለም ገዦች እንዳልነበሩ ያደርጋቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መስፍኖችንም እንዳልነበሩ፥ የምድርንም ፈራጆች እንደ ከንቱ ነገር የሚያደርጋቸው እርሱ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ልዑላንን ያዋርዳል፤ የዚህ ዓለም ገዢዎችንም እንዳልነበሩ ያደርጋቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለቆችንም እንዳልነበሩ፥ የምድርንም ፈራጆች እንደ ከንቱ ነገር የሚያደርጋቸው እርሱ ነው። |
የትዕቢተኞች ሰዎች ዐይኖች ይዋረዳሉ፤ የሰዎችም ኵራት ትወድቃለች፥ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል።
የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን በትዕቢተኛውና በኵራተኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለውም ላይ ይሆናል፤ እነርሱም ይዋረዳሉ፤