እግዚአብሔርም ሕዝቅያስንና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ከአሦር ንጉሥ ከስናክሬም እጅና ከሁሉም እጅ አዳናቸው፤ በዙሪያቸውም ካለው ሁሉ አሳረፋቸው።
ኢሳይያስ 38:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተንና ይህችንም ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ አድናለሁ፤ ለዚችም ከተማ እቆምላታለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተንና ይህችን ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፤ ይህችን ከተማ እከላከልላታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተንና ይህችንም ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፥ ይህችንም ከተማ እጋርዳታለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተንና ይህችን የኢየሩሳሌምን ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፤ ከተማይቱንም በመከላከል እጠብቃለሁ።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተንና ይህችንም ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፥ ይህችንም ከተማ እጋርዳታለሁ። |
እግዚአብሔርም ሕዝቅያስንና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ከአሦር ንጉሥ ከስናክሬም እጅና ከሁሉም እጅ አዳናቸው፤ በዙሪያቸውም ካለው ሁሉ አሳረፋቸው።