Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 38:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 “ሂድ፤ ሕዝ​ቅ​ያ​ስን እን​ዲህ በለው፦ የአ​ባ​ትህ የዳ​ዊት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጸሎ​ት​ህን ሰም​ቻ​ለሁ፤ እን​ባ​ህ​ንም አይ​ቻ​ለሁ፤ እነሆ፥ በዕ​ድ​ሜህ ላይ ዐሥራ አም​ስት ዓመት እጨ​ም​ራ​ለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “ሂድና ለሕዝቅያስ እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ እንባህንም አይቻለሁ፤ በዕድሜህም ላይ ዐሥራ ዐምስት ዓመት እጨምርልሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 “ሂድ፥ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፦ የአባትህ የዳዊት አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፥ እንባህንም አይቻለሁ፤ እነሆ፥ በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “ወደ ሕዝቅያስ ሄደህ እንዲህ በለው፤ ‘እነሆ፥ የቀድሞ አባትህ የዳዊት አምላክ እኔ እግዚአብሔር ጸሎትህን ሰምቼአለሁ፤ እንባህንም አይቼአለሁ፤ ስለዚህም በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት ጨምሬልሃለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ሂድ፥ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፦ የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፥ እንባህንም አይቻለሁ፥ እነሆ፥ በዕድሜህ ላይ አሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 38:5
29 Referencias Cruzadas  

በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና፤ ወደ ሕይወትም ውሃ ምንጭ ይመራቸዋልና፤ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል።”


ክብሬ ይነሣ፥ በበ​ገ​ናና በመ​ሰ​ንቆ ይነሣ፤ እኔም ማልጄ እነ​ሣ​ለሁ።


መል​አ​ኩም እን​ዲህ አለው፥ “ዘካ​ር​ያስ ሆይ፥ አት​ፍራ፤ ጸሎ​ትህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተሰ​ም​ቶ​አ​ልና፤ ሚስ​ትህ ኤል​ሣ​ቤ​ጥም ትፀ​ን​ሳ​ለች፤ ወንድ ልጅ​ንም ትወ​ል​ድ​ል​ሃ​ለች፤ ስሙ​ንም ዮሐ​ንስ ትለ​ዋ​ለህ።


ለወ​ሰ​ኖ​ች​ሽም ሰላ​ምን አደ​ረገ፥ የስ​ን​ዴ​ንም ስብ አጠ​ገ​በሽ።


ነገር ግን ያዘ​ኑ​ትን የሚ​ያ​ጽ​ናና እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቲቶ መም​ጣት አጽ​ና​ናን።


የአ​ሞ​ጽም ልጅ ኢሳ​ይ​ያስ እን​ዲህ ብሎ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ላከ፥ “የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ስለ አሦር ንጉሥ ስለ ሰና​ክ​ሬም ወደ እኔ የለ​መ​ን​ኸ​ውን ሰም​ቻ​ለሁ።


መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜም የሃያ አም​ስት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም የዘ​ካ​ር​ያስ ልጅ አቡ ትባል ነበር።


አሁ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አቤቱ፦ አንተ በፊቴ እንደ ሄድህ ልጆ​ችህ በፊቴ ይሄዱ ዘንድ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውን ቢጠ​ብቁ፥ በፊቴ በእ​ስ​ራ​ኤል ዙፋን የሚ​ቀ​መጥ ሰው ከአ​ንተ አይ​ጠ​ፋም ብለህ ለአ​ባ​ቴ ለ​ዳ​ዊት ተስፋ የሰ​ጠ​ኽ​ውን ጠብቅ።


እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፦ ‘ጳው​ሎስ ሆይ፥ አት​ፍራ፤ በቄ​ሣር ፊት ልት​ቆም ይገ​ባ​ሃል፤ ከአ​ን​ተም ጋር የሚ​ሄ​ዱ​ትን ሁሉ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ንተ ሰጥ​ቶ​ሃል።’


ቍጥር የሌ​ላት ክፋት አግ​ኝ​ታ​ኛ​ለ​ችና፤ ኀጢ​አ​ቶቼ ተገ​ና​ኙኝ፥ ማየ​ትም ተስ​ኖ​ኛል፤ ከራሴ ጠጕር ይልቅ በዙ፥ ልቤም ተወኝ።


በም​ድር ላይ አንድ ቀንም እንኳ ቢኖር፤ ወሮ​ቹም በአ​ንተ ዘንድ የተ​ቈ​ጠሩ ናቸው፤ ዘመ​ኑ​ንም ወስ​ነህ ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ፤ እር​ሱም ከዚያ አያ​ል​ፍም።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም በነ​ገሠ በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ዓመት የአ​ሦር ንጉሥ ሰና​ክ​ሬም ወደ ይሁዳ ወደ ተመ​ሸ​ጉት ከተ​ሞች ሁሉ ወጣ፤ ወሰ​ዳ​ቸ​ውም።


ነገር ግን ልጁን ከእ​ርሱ በኋላ ያስ​ነሣ ዘንድ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ያጸና ዘንድ አም​ላኩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ዳዊት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መብ​ራ​ትን አደ​ረ​ገ​ለት፤


በነ​ገ​ሠም በስ​ም​ን​ተ​ኛው ዓመት ገና ብላ​ቴና ሳለ የአ​ባ​ቱን የዳ​ዊ​ትን አም​ላክ ይፈ​ልግ ጀመረ፤ በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ይሁ​ዳ​ንና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ከኮ​ረ​ብ​ታ​ውና ከዐ​ፀ​ዶቹ፥ ከተ​ቀ​ረ​ጹ​ትና ቀል​ጠው ከተ​ሠ​ሩት ምስ​ሎች ያነጻ ጀመር።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ ኢሳ​ይ​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልመ​ና​ዬን ሰማኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸሎ​ቴን ተቀ​በለ።


ለመ​ግ​ደል ጊዜ አለው፥ ለመ​ፈ​ወ​ስም ጊዜ አለው፤ ለማ​ፍ​ረስ ጊዜ አለው፥ ለመ​ሥ​ራ​ትም ጊዜ አለው፤


የአ​ሞጽ ልጅ ኢሳ​ይ​ያ​ስም ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ተላከ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ስለ አሦር ንጉሥ ስለ ሰና​ክ​ሬም ወደ እኔ የጸ​ለ​ይ​ኸ​ውን ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ።


አንተ ድም​ፄን ሰማህ፤ ጆሮ​ህ​ንም ከል​መ​ናዬ አት​መ​ልስ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios