ኢሳይያስ 38:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ወራት እስኪነጋ ድረስ እንደ አንበሳ ታወክሁ፤ እንደዚሁም አጥንቶች ተቀጠቀጡብኝ፤ ከማለዳ ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ተጨነቅሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስከ ማለዳ በትዕግሥት ጠበቅሁ፤ እርሱ ግን እንደ አንበሳ ዐጥንቶቼን ሁሉ ሰባበረ፤ ከጧት እስከ ማታም ልትጨርሰኝ ፈጠንህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስኪ ነጋ ድረስ ቈይቼ ነበር፤ እርሱ እንደ አንበሳ አጥንቴን ሁሉ ሰበረ፤ ከጠዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ፍጻሜዬን አቀረብከው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስከ ንጋት ድረስ ስጮኽ ዐድራለሁ፤ እንደ አንበሳም አጥንቶቼን ሁሉ ሰባበርክ፤ ሌሊትና ቀንም ለሥቃይ አሳልፈህ ሰጠኸኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስኪነጋ ድረስ ቈይቼ ነበር፥ እርሱ እንደ አንበሳ አጥንቴን ሁሉ ሰበረ፥ ከማለዳ ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ታጠፋኛለህ። |
ቅንነትህን በልቤ ውስጥ አልሰወርሁም፥ ማዳንህንም ተናገርሁ፤ ይቅርታህንና ምሕረትህን ከታላቅ ጉባኤ አልሰወርሁም።
እኔስ በእግዚአብሔር ቤት እንደ ለመለመ እንደ ወይራ ዛፍ ነኝ፤ ለዓለምና ለዘለዓለም በእግዚአብሔር ምሕረት ታመንሁ።
እኔም ለኤፍሬም እንደ ነብር፥ ለይሁዳም ቤት እንደ አንበሳ ደቦል እሆናለሁና፤ እኔም ነጥቄ እሄዳለሁ፤ እወስድማለሁ፤ የሚያድናቸውም የለም።