La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 37:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ሱም፥ “የኢ​ት​ዮ​ጵያ ንጉሥ ቲር​ሐቅ ሊዋ​ጋህ መጥ​ቶ​አል” የሚል ወሬ ሰማ። በሰ​ማም ጊዜ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ እን​ዲህ ሲል፦

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ደግሞም ሰናክሬም፣ የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ ሊወጋው መምጣቱን ሰማ፤ ይህንም እንደ ሰማ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞች ላከ፤ እንዲህም አለ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የአሦርም ንጉሥ፦ “የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ ሊዋጋህ መጥቷል” የሚል ወሬ ሰማ። ይህን በሰማም ጊዜ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ፥ እንዲህም አለው፦

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በኢትዮጵያ ንጉሥ በቲርሃቃ የሚመራ የግብጽ ሠራዊት እነርሱን ለመውጋት በመገሥገሥ ላይ መሆኑን አሦራውያን ሰሙ፤ የአሦር ንጉሥ ይህን በሰማ ጊዜ ወደ ሕዝቅያስ እንዲህ የሚል ደብዳቤ በመልእክተኛ እጅ ላከ፦

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱም፦ የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ ሊዋጋህ መጥቶአል የሚል ወሬ ሰማ። በሰማም ጊዜ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ፥ እንዲህ ሲል፦

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 37:9
7 Referencias Cruzadas  

አክ​ዓ​ብም ናቡ​ቴን፥ “በቤቴ አቅ​ራ​ቢያ ነውና የአ​ት​ክ​ልት ቦታ አደ​ር​ገው ዘንድ የወ​ይን ቦታ​ህን ስጠኝ፤ ስለ እር​ሱም ከእ​ርሱ የተ​ሻለ የወ​ይን ቦታ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ ወይም ብት​ወ​ድድ ዋጋ​ውን ወርቅ እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ” ብሎ ተና​ገ​ረው።


የአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት ምን ይመ​ል​ሳሉ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽዮ​ንን መሠ​ረ​ታት፤ ትሑ​ታን የሆ​ኑ​ት​ንም ሕዝብ አዳ​ና​ቸው።


በኢ​ት​ዮ​ጵያ ወን​ዞች ማዶ ላለች፥ ክንፍ ያላ​ቸው መር​ከ​ቦች ላሉ​ባት ምድር ወዮ​ላት!


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “ባሪ​ያዬ ኢሳ​ይ​ያስ ሦስት ዓመት ራቁ​ቱን በባዶ እግሩ እንደ ሄደ፥ እን​ዲሁ በግ​ብ​ፅና በኢ​ት​ዮ​ጵያ ላይ ሦስት ዓመት ምል​ክ​ትና ተአ​ም​ራት ይደ​ረ​ጋል።


ግብ​ፃ​ው​ያን ከኢ​ት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያን ጋር ይሸ​ነ​ፋሉ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ከታ​መ​ኑ​ባ​ቸው ጋር ይፈ​ራሉ፤ ያፍ​ሩ​ማል።


እነሆ፥ መን​ፈ​ስን በላዩ እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ወሬ​ንም ይሰ​ማል፤ ወደ ምድ​ሩም ይመ​ለ​ሳል፤ በም​ድ​ሩም በሰ​ይፍ እን​ዲ​ወ​ድቅ አደ​ር​ጋ​ለሁ በሉት” አላ​ቸው።